በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ለሦስተኛ ቀን በቀጠለው ውጊያ ቢያንስ 185 ሰዎች ተገደሉ

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:38 0:00

በሱዳን፣ በጦር ሠራዊቱ እና በፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሉ መሀከል የተቀሰቀሰው ውጊያ፣ ዛሬ ለአራተኛ ቀን የቀጠለ ሲኾን፣ በዋና ከተማዋ ካርቱም ከባድ ውጊያ እየተካሔደ ይገኛል፡፡ በመዲናዋ በሚገኘው የጦር ሠራዊቱ ዋና መሥሪያ ቤት፣ በካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ እና በቤተ መንግሥቱ አካባቢ ከባድ ውጊያ ተካሒዷል፡፡ የአገሪቱ የሐኪሞች ማኅበር እንዳስታወቀው፣ በውጊያው እስከ አሁን ድረስ ቢያንስ 185 ሰዎች ተገድለዋል፡፡

ተፋላሚዎቹ ወገኖች ውጊያውን እንዲያቆሙ ተማጽኖው ቀጥሏል፡፡ ማይክል አቲት ከኻርቱም ያጠናቀረውንና ሌሎችንም ዘገባዎች አጠናቅራ፣ ቆንጅት ታየ ተከታዩን ዘገባ አሰናድታለች፡፡

XS
SM
MD
LG