በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ለ24 ሰዓት ተኩስ ማቆም ስምምነት ተደረሰ 


የሱዳን ሠራዊት እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (አር ኤስ ኤፍ ) በካርቱም እያደረጉት ባለው ፍልሚያ ከካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ የወጣው ጭስ።
የሱዳን ሠራዊት እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (አር ኤስ ኤፍ ) በካርቱም እያደረጉት ባለው ፍልሚያ ከካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ የወጣው ጭስ።

በመፋለም ላይ ያሉት የሱዳን ሠራዊት እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (አር ኤስ ኤፍ ) ለ 24 ሠዓት ተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የአረብኛ ቋንቋ ቴሌቭን ጣቢያዎች በመዘገብ ላይ ናቸው።

ሻምስ ኤል ዲን ካባሺ የተባሉ የሱዳን ከፍተኛ የጦር መሪ ሠራዊቱ የ24 ሰዓቱን ተኩስ እንደሚያከብር አል አራቢያ እና አል ጃዝዚራ ለተሰኙት ቴሌቭዥን ጣቢያዎች መናገራቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ በሪፖርቱ አመልክቷል።

የአንድ ቀኑን ተኩስ ማቆም ሠራዊቱ እንደሚያከብር ሲ.ኤኔ.ኤን አረብኛ የአገሪቱን ጦር አዛዥ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ጠቅሶ ዘግቧል ።

ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በሱዳን ሠራዊትና በፈጥኖ ደራሽ ኃይል ወይም አር ኤስ ኤፍ መካከል ሲደረግ የቆየው ውጊያ የሱዳን መዲና ካርቱምንና ሌሎች ስፍራዎችን ትርምስ ውስጥ ከቷቸዋል።

በመዲናዋና በሌሎች ከተሞች የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ቤታቸው ለመደበቅ ተገደዋል።

ሁለቱ ተቀናቃኝ ጄኔራሎች፣ የሠራዊቱ አዛዥ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን እና የአር ኤስ ኤፍ አዛዥ ጀነራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወይ ኽመቲ አንዱ ሌላውን ለመሰምሰስ በመዛት ላይ ናቸው።

XS
SM
MD
LG