በምሥራቅ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ውስጥ ከሃምሣ ሚሊየን በላይ ሰው በማስጠንቀቂያና በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ሥር እንዲኖር ያደረገው እጅግ የበረታው ንፋስና ከባድ ዝናብ ኃይሉን እየጨመረና የሚሸፍነውን አካባቢ እያሰፋ ነው፡፡
የመጨረሻው “እሰጣገባ” ተካሄደ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና ሪፐብሊካኑ ዕጩ ተፎካካሪያቸው ሚት ራምኒ በጉጉት ሲጠበቅ የሰነበተውን ሁለተኛውን ክርክራቸውን ማክሰኞ፣ ጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም ምሽት ላይ አካሂደዋል፡፡
የፊታችን ጥቅምት 27 ቀን 2005 ዓ.ም ለሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ አጠቃላይ ምርጫ የሚደረገው ፕሬዚንዳታዊ ፉክክርና ዘመቻ አካል የሆነው የዕጩዎቹ ምክትል ፕሬዚዳንቶች የፊት ለፊት ክርክር ሐሙስ፤ ጥቅምት 1 ምሽት ላይ ተካሂዷል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎች በኢትዮጵያ ላይ ስለሚከተሉት ፖሊሲ የሚያስረዱበት ስብሰባ የፊታችን ዕሁድ ቨርጂንያ ውስጥ ይካሄዳል፡፡
የክርክር ተጨባጭ ሚናና ይዘት፤ እንዲሁም በፕሬዝዳንት Obama እና በተፎካካሪያቸው Mr Romney መካከል የተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ክርክር ይፈተሻል።
የፊታችን ጥቅምት 27/2005 ዓ.ም ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚፎካከሩት የዴሞክራቲክ ፓርቲው ዕጩ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና የሪፐብሊካን ፓርቲው ዕጩ የቀድሞ የማሳቹሴትስ ገዥ ሚት ራምኒ የመጀመሪያውን የፊት ለፊት ክርክር አካሄዱ፡፡
ሥልጣን የጨበጡ ሁሉ የእውነተኛ ዴሞክራሲ፣ የእውነተኛ ነፃነት ግንባታ ከባድ እንደሆነ ተገንዝበው በተቃውሞ ላይ ማሣደድና አፈና እንዳያካሂዱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አሳሰቡ፡፡
ጥቅምት 27 / 2005 ዓ.ም ለሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ አጠቃላይ ምርጫ ዴሞክራቲክ ፓርቲው ለፕሬዚዳንትነት እንዲወዳደሩ ያጫቸው ባራክ ኦባማ ዕጩነታቸውን መቀበላቸውን በትናንት ምሽቱ የፓርቲያቸው ጉባዔ ላይ በይፋ አሣውቀዋል፡፡