ቪዥን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰበተኛ የጥናትና ምርምር ጉባዔውን አዲስ አበባ ላይ ከፈተ፡፡
ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ውስጥ የፊታችን ዕሁድ ይካሄዳል ከተባለው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጭ እንዲሆኑ መወሰኑ ያስቆጣቸው የሃገሪቱ ምሥራቃዊ አካባቢዎች ነዋሪዎች ያደረጉትን ሰልፍ ለመበተን ፖሊስ ዛሬ በወሰደው ዕርምጃ በተቃዋሚዎች ላይ ቀጥተኛ ተኩስ መክፈቱና አስለቃሽ ጋዝ መርጨቱ ተዘግቧል።
በሰሜን አሜሪካ ጉብኝት ያደረገው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የልዑካን ቡድን ወደ አገር ከመመለሱ በፊት ከቪኦኤ ጋር ተወያይቷል። የልዑካን ብድኑ መሪና የክልሉ መንግሥት ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ስቱዱያችን በመገኘት በተለያዩ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ምላሽ ሰጥተውናል፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንትና የልዑካን ቡድኑ መሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት መግለጫ፣ ተልዕኳቸው የተሳካ እንደነበር ገልፀው፡፡
''የህክምና ባለሙያዎች ምንም ያህል ኑሮዋችህ አስደሳች ባይሆን እና ተጎጂ ብትሆኑም እናት እናት ነች፣ ሀገርም ሀገር ነው። የተመመው አባታችን፣ የታመመችው እናታችን ናት እነሱን መርዳት ይኖርብናል - '' ዶ/ር ሰኚ ቀጄላ፡፡ በልጅነቴ ሆስፒታል አካባቢ ተወልጄ ማደጌ፣ የሕሙማንን ችግር ማየቴ፣ ጤናን እንድማር ውስጤ ተፅዕኖ ፈጥሮብኛል። አሁን የሀገሩን ከፍተኛ ነጥብ 3.95 ባስመዘግብም፣ ተስፋ የቆረጥኩበትም ወቅት ነበር።
በኢትዮጵያ ከየትኛውም ጉዳይ በላይ መቅደም ያለበት አገርን ማረጋጋትና ሰላምን ማስፈን ነው ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት አስታወቀ።
“ኤልሻዳይ የእርዳታና የልማት ድርጅት በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት 'ከልመናና ከጎዳና ህይወት እናወጣችኃለን' በሚል ሰበብ ከጎዳና ላይ ታፍሰንና ተጋፈን ወደ ማሰልጠኛ ተቋም ብንወሰድም፤
ከዘጠኝ ክልሎች የተወጣጡ ሃያ ሁለት እናቶች - በባህር ዳር
የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረመስቀል ጉብኝቱን አስመልክተው በትዊተር መልዕክታቸው ሲገልጹ፣ "የኤርትራና ሶማልያ ግንኙነት፣ በወዳጅነት፣ በመከባበርና በአብሮነት ላይ የተመሠረተ ነው" ብለዋል።
በመቀሌ ከተማ ህገ መንግሥት ይከበር የሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ የህዝብ ድምፅ አለ መስማት ከባድ ዋጋ ያስከፍላል ብለዋል። በሰልፉ ላይ ሕገ መንግሥት ይከበር፣ ብሄር ተኮር ጥቃት ይቁም እንዲሁም የውጭ ጣልቃ ገብነት ይቁም የሚሉ መፈክሮች ተደምጧል።
በጣና ቂርቆስ ገዳም የሚኖሩ መነኮሳት በእንቦጭ አረም ምክንያት ህልውናችን አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉ ተናገሩ።
በዓለማችን ዙሪያ የሚገኙ ወጣት የእግር ኳስ ተጫዋቾች፣ ጀግና የሚሏቸው ኮከብ ተጫዋቾች የደረሱበት ትልቅ ደረጃ የመድረስ ተስፋ ሰንቀው ወደ አውሮፓ በመጓዝ እንደ ባርሴሎና ላሉ ታዋቂ ቡድኖች ለመጫወት ይፈልጋሉ። በዚህ ረገድ፣ አብዛኞቹ ከአፍሪካ የሆኑ ፍልሰተኞች የመጀመሪያውን ዕርምጃ ወስደዋል። በአንድ አዛኝ አሰልጣኝ ዕርዳታ አማካይነትም አፍሪካውያኑ ወጣቶች በስፔኑ ሊግ ውስጥ ቡድን መሥርተዋል።
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ራይነር ዛሬ ከሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሙስጣፋ ሞሐመድ ጋር በክልሉ ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም በልማት ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል። የተለያዩ የልማት ተቋማትንም ጎብኝተዋል። በቦታው የሚገኘውን የአሜሪካ ድምፅራድዮ ዘጋቢ መላስካቸው አመሀን ስለጉብኝቱ እንዲያብራራልን አነጋግረነዋል።
ጠ/ር አብይ አሕመድ፣ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እናየሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ አመሻሹን ባህርዳር ከተማ ገብተዋል፡፡ መሪዎቹ ባህርዳር ከተማ ሲደርሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አደርገውላቸዋል።
የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ተከፍቶ የንግድ ልውውጥ፣ ቱሪዝምና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ከሃያ ዓመታት በኋላ በአዲስ ተጀምሯል፡፡
የትግራይ ተወላጅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለደኅንነታችን እንሰጋለን ሲሉ ወደ ሌሎች የሃገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይ ወደ አማራ ክልል አንሄድም፣ እዚሁ ክልላችን ውስጥ እንመደብ ሲሉ በቅርቡ መቀሌ ከተማ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ተዘግቧል። በትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ስለዚሁ ተጠይቀው፣ “በቂ ዝግጅት ስለተደረገ የሚያስፈራ ምክንያት የለም” ብለዋል።
“ሴቶች በነበረው ነውጥ ውስጥ ሀገር ተረጋግታ እንድትራመድ አስተዋፅዖ ያበረከቱ በንፅፅር በሌብነት ባነሰ ደረጃ የሚታሙ ናቸውና” ጠ/ሚ አብይ አሕመድ። “በሴቶቻችን ዕምነት ሊኖረን ይገባል። አጋጣሚ ሆኖ በታሪካችን ብዙ ትልልቅ ሥፍራ ሳያገኙ ቀርቷል። የወንድ ተፅዕኖና የወንድ ዓለም አንደመሆኑ።” የአፍሪካ ኢንሽዪቲቭ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር አቶ ክቡር ገና።
ቱርክ የምዕራባዊ የባህር ጠረፍ ሠላሳ ሥምንት የሚጠጉ ፍልሰተኞችን የጫነች ጀልባ ተገልብጣ ሥምንት ሰዎች ሕይወታች ሲያልፍ፣ ሃያ አምስት ሰዎች የት እንደገቡ ማወቅ እንዳልተቻለ ተገለፀ፡፡ የቱርክ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች እንደገለፁት በባለፈው ዕሮብ አደጋው መከሰቱን፣ ድብዛቸው የጠፉንት ፍልሰተኞች ፍለጋውን መቀጠሉን አስታውቋል፡፡ ከአፍሪካና ከመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት የሚነሱ ፍልሰተኞች ቱርክን ወደ ሌሎች አውሮፓ ሀገራት ለመሸጋገሪያ መንገድ ይጠቀሟታል፡፡
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ አዲስ አበባ ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባበል፡፡
ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድና ምክትል ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሀገር መከላከያ የተለያየ ክፍለ ጦር ከተውጣጡ የጦር ሰራዊት አባላት ጋር ትናንት ተወያይተዋል። Ethiopian Soldiers Protesting Over Pay Meet With PM
ዛሬ በኬንያ ምዕራባዊ ክፍል ኪስሙ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ ቢያንስ የሃምሳ ስዎች ሕይወት ማለፉ ተገለፀ:: ሠላሳ አንድ ወንዶች፣ አሥራ ሁለት ሴቶችና ሰባት ሕጻናት መሆኑንም የአካባቢው ፖሊስ ጠቁሟል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ