የኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አርሰዲ ተከብሮ ውሏል
በአፍሪካ የሚገኙ ስደተኞች መብታቸው እንዲጠበቅ የዓለምቀፉ የስደተኞች ድርጅት /ዩኤንኤችሲአር/ አዲስ ዘመቻ ጀምሯል። ድርጅቱ ዘመቻውን በ5 የአፍሪካ ሀገሮች የጀመረ ሲሆን፣ ግለሰቦች እንዲሁም የአፍሪካ አህጉር በቀል ድርጅቶች ለስደተኞች ድጋፍ እንዲያደርጉ የሚያበረታታ ዘመቻ ነው። ዩኤንኤችሲአር ‘ሉኩሉኩ’ በመባል የሚታወቀውን ይህንን ዘመቻ ለአፍሪካዊያን በተለያዩ መንገድ እያስተዋወቀ መሆኑን ገልጿል።
13ኛው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጉባዔ በዛሬው ዕለት በመቀሌ ተጀምሯል።
የኢትዮጵያና የኤርትራ ነጋዴዎች አስመራ ውስጥ አዲስ በተሰጣቸው ጊዜያዊ መገበያያ "መነሃሪያ" ተብሎ በሚጠራ ሥፍራ ሸቀጦቻቸውን ለገበያተኞች ያቀርባሉ፡፡
የአውሮፓ ሕብረት ሀገሮች መሪዎች በስደተኞች ጉዳይ ላይ በነገው ዕለት በኦስትሪያ ከተማ በሣልዝበርግ ሊያደርጉት የታቀደው ጉባዔ በአባል ሃገራቱ መካከል የተፈጠረው ጥልቅ መከፋፈል ሊያደናቅፈው እንደሚችል ተሰግቷል። ብራሰልስ የምትፈልገው የአውሮፓ ሕብረት የድንበር ጠባቂዎች ወደሌሎቹ ሀገሮች ዘልቀው በመግባት እንዲመደቡ ሲሆን ሌሎች እንደ ሃንጋሪ ያሉ አባል ሀገሮች ፍላጎት ግን የራሣቸውን ድንበር በራሣቸው ወታደሮች ማስጠበቅ ነው።
በቡራዩና አካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የ23 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ትናንት ሰኞ የተካሄደ ሠላማዊ ሰልፍ፡፡
ላለፉት 8 ዓመታት በኤርትራ ሀሪና እየተባለ በሚጠራው የጦር ሰፈር ካንፕ ገንብቶ ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሲታገል የነበረው የአማራ ዴምክራሲ ኃይል ንቅናቄ /አዴኃን/ ዛሬ በባህር ዳር በመገኘት ሰላማዊ ትግል ለማድረግ መወሰኑን ገልፆል።
በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ዛላንበሳ አካባቢ፣ የሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች አዲስ ዓመትን በጋራ አከበሩ፡፡ ለሀያ ዓመታት ተለያይተው የነበሩ ቤተሰቦችም ተገናኝተዋል።
የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ፎረም ከነገ ጀምሮ በክልል ዋና ከተሞችና በአዲስ አበባ የሚካሄድ ውይይቶች ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለጠ/ሚ አብይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ ትናንት ሰኞ ለአፍሪካ ሃገሮች ስድሳ ቢሊዮን ዶላር መደቡ። ድኅነት ጠና ላለባቸው ሃገሮች ደግሞ የተወሰነውን ዕዳ ሰርዘውላቸዋል።
ትላንት በእሳት ጋይቶ ከወደመው የብራዚል ብሄራዊ ቤተ መዘክር የተረፈ ነገር ካለ ለማየት የእሳት አደጋ ሰራተኞች እየፈለጉ ናቸው። የማይተኩ የሀገሪቱን ታሪክ የሚያንፀባርቁ ሰፊ ይዘት የነበራቸው የቅርሳቅርስ ስብስቦች በነው በመቅረታቸው የሀገሪቱ ህዝብ ከፍተኛ ሀዘን እንደተሰማው ተገልጿል።
የፈረንሣይ ዋና ከተማ ፓሪስ በአሁኑ ጊዜ በሀገር ጎብኚዎች የምትጥለቀለቅበት ወቅት ነው።
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የኢድ አል አደሃን በዓል ሲያከብር፣ አንድነቱን በማጠናከር እና ይቅርታን በማብዛት እንዲያከብር ጥሪ ቀርቧል።
ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ ቁጥራቸው 125 የሚሆኑ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጭ ወጣቶች በባህር ዳር ከተማ ዙሪያ ልዩ ስሙ ሰባት አሚት በተባለ አካባቢ በአባይ ወንዝ ላይ የእምቦጭ አረምን የማስወገድ ሥራ ሰርተዋል፡፡
ዛሬ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችንና ሁከቶችን ለመግታት የኢህአዴግ የካድሬ አስተዳደር መለወጥ አለበት ሲል የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ አስታወቀ፡፡ በሚቀጥለው ሀገርቀፍ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ለመመስረት ከወዲሁ የብሄራዊ አንድነት መንግሥት እንዲቋቋምም ጠየቀ፡፡
ጥቃቱ የተፈፀመው የዛሬ 20 ዓመት ነሐሴ 7/1998 ሲሆን በጊዜዉ ከ250 በላይ ሰዎች ሕይወታቸዉ ማለፉ የሚታወስ ነው።
በዕርቀ ሠላም መርሃ ግብሩ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ የተለያዩ ሀይማኖት መሪዎች፣ አምባሳደሮች ተገኝተዋል፡፡
“.. ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በሌለበት የማገልገል ፍላጎት የለንም። .. በግድ ማስተዳደር ምን እንደሚመስል ግን አይተናል።..” ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ።
የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል በኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን አሰታወቁ፡፡ የትግራይ ክልል መስተዳድርና በግላቸው ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ እንደወሰኑ ለጋዜጠኞች አስታወቁ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ