ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች በተካሄዱ ግጭቶች ሳቢያ፡ የሰው ሕይወት መጥፋቱና ብዙዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወቃል። የውጥረቱ አሳሳቢነት የኢትዮጵያን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የዓለሙን ህብረተሰብ ትኩረት እንደሳበ መሆኑ ይዘገባል።
በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚቀርቡ የውሣኔ ሀሳቦችን «በተሳካ ሁኔታ አምክኛለሁ» ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ቢናገርም ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ህጎች አሁንም በኮንግረሱ እየረቀቁ መሆናቸውን የህዝብ ተወካዮች አመልክተዋል።
በሪዮ ኦሊምፒክስ ሁለት እጆቹን አጣምሮ ከግንባሩ በላይ በማሳየት በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የመብት ጥሰቶችን ለዓለም ግንዛቤ ያስጨበጠው ኢትዮጵያዊ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከቤተሰቦቹ ጋር ተቀላቀለ።
በዩናይትድ ስቴትስ የስልጣን ሽግግርና በአፍሪካ ሃገሮች ደህንነት ላይ ያተኮረ ውይይት ባለፈው ዓርብ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ተካሂዷል።
የዋሺንግተን ዲሲና የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ሜሪላንድ ግዛት ውስጥ በሚገኘው አርቲሜዥያ ሃይቅ ላይ ከአሥራ አምስት ዓመታት በላይ እየተከበረ ያለ ወግና ልማድ የሆነው የእሬቻ በዓል ዛሬ እየታሰበ ያለው ከወትሮ በተለየ ሁኔታ በኀዘን መንፈስ መሆኑን ከአዘጋጆቹ አንዱ የሆኑት አቶ በቀለ ቶሎሣ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
የቅዱስ ሮማዳን ወር ማብቂያ የሆነው 1437ኛው ኢል አል ፍጥር ዛሬ በመላ ዓለም ሙስሊሞች ዘንድ እየተከበረ ነው፡፡
በዚህ ሳምንት በሞት የተለየው አድማሱ ብርሃኑ ስራዎች ቀልድ በአንድ ማህበረሰብ ህልውና፣ የለት ተለት ኑሮና ማንነት ላይ ያለውን ሚና ያጎላሉ።