በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች ግጭቶች ጉዳይ - ኒኮላስ ባርኔት

U.S. Embassy Addis Ababa
U.S. Embassy Addis Ababa

ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች በተካሄዱ ግጭቶች ሳቢያ፡ የሰው ሕይወት መጥፋቱና ብዙዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወቃል። የውጥረቱ አሳሳቢነት የኢትዮጵያን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የዓለሙን ህብረተሰብ ትኩረት እንደሳበ መሆኑ ይዘገባል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች በተካሄዱ ግጭቶች ሳቢያ፡ የሰው ሕይወት መጥፋቱና ብዙዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወቃል። የውጥረቱ አሳሳቢነት የኢትዮጵያን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የዓለሙን ህብረተሰብ ትኩረት እንደሳበ መሆኑ ይዘገባል።

የተባበሩት መንግሥታት ዓለምአቀፉ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት /IOM/ ትላንት ባወጣው ሪፖርት መሠረት፡ ከግጭቶች ጋር በተያያዘ በአሁኑ ወቅት የሚደርሰው የዜጎች መፈናቀል፡ ከመቼውም በበለጠ ተስፋፍቷል።

የዓለሙ ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ /OCHA/ ያወጣው ሪፖርት፡ እ አ አ ከ 2015 ወዲህ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች በተካሄዱ ግጭቶች ሳቢያ የተፈናቁሉ ሕዝቦች 1 ሚሊዮን አካባቢ እንደሚደርስ ይጠቁማል።

ከዓለም ከፍተኛ እርዳታ ለኢትዮጵያ የምትለግሰው ዩናይትድ ስቴትስ ይህን በሃገሪቱ የተከሰተውን የብሄረሰቦች ግጭት የምታየው እንዴት ነው? መፍትሄ ለማምጣትስ ጥረት ታደርጋለች?

ባልደረባችን ትዕግስት ገሜ፡ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ቃል አቀባይ የሆኑትን ኒኮላስ ባርኔት አነጋግራለች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች ግጭቶች ጉዳይ - ኒኮላስ ባርኔት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:20 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG