በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያዊያን የኢድ አል ፍጥር አከባበር


የኢድ አል ፍጥር አከባበር- አዲስ አበባ
የኢድ አል ፍጥር አከባበር- አዲስ አበባ

የቅዱስ ሮማዳን ወር ማብቂያ የሆነው 1437ኛው ኢል አል ፍጥር ዛሬ በመላ ዓለም ሙስሊሞች ዘንድ እየተከበረ ነው፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የእሥልምና መሪዎች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ እሥልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሼኽ ዑመር ኢማም ዑመር ባስተላለፉት መልዕክት የፆሙ ወቅት የተመቸ እንደነበር አመልክተው ሙስሊም መልካም ተግባር የሚፈፅመው በራማዳን ብቻ ሳይሆን “ከራማዳን ያገኘነውን ጥሩ ባሕርይና ጥሩ ልምድ ወደፊትም አስቀጥለን አላህ የሚወድዳቸውን ሥራ ሁሉ ሙስሊም እንዲሠራ የሚል መልዕክት አስተላልፋለሁ” ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሳውዲ ዐረቢያ ጅዳ ከተማ ነዋሪ የእስልምና መምሕረ ሼሕ ሞሐመድ ዘዪን ሰሞኑን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ስለተፈጸሙ ጥቃቶች ፤ “በእስላም እንዲህ ያሉ ጥፋቶች ከመነሻው የተወገዙ ናቸው። እንኳንስ የሰውን ልጅ መግደል አይደለም መስደብና መገላመጥ እንኳን ትልቅ ወንጀል ሃይማኖት ነው እስልምና።” ብለዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ጉዳዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሼክ ኡመር ኢማም ኡመር ተመሳሳይ ሃሳብ ሰጥተዋል።

ዒድ ኣልፈጥር በኣስመራ
ዒድ ኣልፈጥር በኣስመራ

የዛሬው ኢድ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ እንዴት እንደተከበረ አስተያየታቸውን የሰጡ ሰዎች አሉ።

ኢድ አልፈጥር በዋሽንግተን ዲሲ
ኢድ አልፈጥር በዋሽንግተን ዲሲ

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የኢትዮጵያዊያን የኢድ አል ፍጥር አከባበር
please wait

No media source currently available

0:00 0:26:38 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG