ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
የዋሺንግተን ዲሲና የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ሜሪላንድ ግዛት ውስጥ በሚገኘው አርቲሜዥያ ሃይቅ ላይ ከአሥራ አምስት ዓመታት በላይ እየተከበረ ያለ ወግና ልማድ የሆነው የእሬቻ በዓል ዛሬ እየታሰበ ያለው ከወትሮ በተለየ ሁኔታ በኀዘን መንፈስ መሆኑን ከአዘጋጆቹ አንዱ የሆኑት አቶ በቀለ ቶሎሣ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
የዘንድሮው እሬቻ ቢሾፍቱ ከሚገኘው ሆራ አርሰዴ ክብረ በዓል ጋር በአንድ ቀን መዋሉን የጠቀሱት አቶ በቀለ የኦሮሞ ማኅበረሰብ በዓሉን አሜሪካ ውስጥ የሚያከብረው የሕዝቡን ባሕልና ወግ ጠብቆ ለማቆየት እንደሆነ አመልክተዋል፡፡
ዛሬ ቢሾፍቱ ላይ በተፈጠረው ሁኔታ ያዘነው የበዓሉ ታዳሚ ሃገር ቤት ካለው ወገኑ ጋር መሆኑን በሚገልፅ ሁኔታ እንደሚያከበብርም አዘጋጁ አክለው አመልክተዋል፡፡
አቶ በቀለ ቶሎሣ ከቪኦኤ ጋር የደረጉትን አጭር ቃለ ምልልስ የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡