በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቀልድና ቁምነገር በኦሮሚኛ ኮሜዲያን አድማሱ ብርሃኑ ህይወት


በዚህ ሳምንት በሞት የተለየው አድማሱ ብርሃኑ ስራዎች ቀልድ በአንድ ማህበረሰብ ህልውና፣ የለት ተለት ኑሮና ማንነት ላይ ያለውን ሚና ያጎላሉ።

አድማሱ ብርሃኑ በአድናቂዎቹ አባ ለታ-አባ ካሩ በመባል ነው የሚታወቀው። እነዚህም በስራዎቹ የተጫወታቸው ገጸ-ባህርያት ናቸው።

በተለይ በ1980ዎቹ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ደንጋ የቅዳሜ መዝናኛ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል። ኦሮሚኛ ቋንቋ የማይችሉ ሁሉ የአድማሱን ቀልዶች፤ በትወናው፤ ለየት ባለችው ቅጭሞ ፊቱ ይወዱለታል፤ እንዲያውም የማይናገሩትን ቋንቋ እንደሚናገሩና እንደሚሰሙ እንዲያስቡ የማድረግ ችሎታ አለው።

አባ ለታ በዜማ፣ በትረካና በቴሌቭዥን ድራማዎቹ፤ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መልእክቶችን ያደረሰ፤ ግሩም የኪነጥበብ ሰው ነው።

አባ ለታ ድንገት ነው ያረፈው። በኦሮሚያ ቴሌቭዥን የሚተላለፍ ጤቡ የተባለ ድራማ ላይ በመተወን ላይ ነበር። ፕሮግራሙን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

ቀልድና ቁምነገር በኦሮሚኛ ኮሜዲያን አድማሱ ብርሃኑ ህይወት
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG