የኢትዮጵያ ሯጮች በምርመራ ላይ መሆናቸው ተዳምሮ፥ በመጪው የሪዮ ኦሊምፒክ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል የሚል ፍራቻ ነግሷል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የሩሲያ አትሌቶች ከማናቸውም ዓለምአቀፍ የሩጫ ውድድሮች የታገዱ ሲሆን፥ የኬንያ አትሌቶች ተመሳሳይ እጣእንዳይደርሳቸው ተሰግቷል።
አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ሯጮች በምርመራ ላይ መሆናቸው ተዳምሮ፥ በመጪው የሪዮ ኦሊምፒክ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል የሚል ፍራቻ ነግሷል።
በሌላ በኩል የዓለም ሻምፒዮናዎች ኢትዮጵያ እያዊቷ ገንዘቤ ዲባባና ጃማይካውያኑ ኡሴን ቦልትና ሼሊ-አን ፍሬዘር-ፕራይስ፥ ለ 2016 Laureus ሽልማት ታጭተዋል። ላውረስ (The Laureus World Sports Awards) በስፖርት ውድድሮች በዓለማችን ከፍተኛውን ድል ላስመዘገቡ ስፖርተኞች ክብር በመስጠት ይታወቃል።
የዘንድሮውንሽልማት ሥነ-ሥርዓት ከአንድ ወር በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በርሊን፥ ጀርመን ውስጥ ያደርጋል።
Your browser doesn’t support HTML5