በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ገንዘቤ ዲባባ ለ26 ዓመታት ተይዞ የቆየውን የአንድ ማይል የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች

  • ሰሎሞን ክፍሌ

ገንዘቤ ዲባባ በስቶክሆልም - ፋይል ፎቶ

ገንዘቤ ዲባባ ስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ አዲስ ያስመዘገበችው የዓለም ክብረ ወሰን 4 13 31 ሲሆን ላለፉት 26 ዓመታት ሳይደፈር ከቆየው ጊዜ ላይ አምስት ሴኮንዶች ግድም ላጭታለታለች።

ገንዘቤ ዲባባ በአዳራሽ ውስጥ ሩጫ ውድድር ለ 26 ዓመታት ተይዞ የቆየውን የአንድ ማይል የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች። ባሁኑ ወቅት 5 የዓለም ሬኮርድ ባለቤት ነች።

ገንዘቤ ዲባባ ስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ አዲስ ያስመዘገበችው የዓለም ክብረ ወሰን 4 13 31 ሲሆን ላለፉት 26 ዓመታት ሳይደፈር ከቆየው ጊዜ ላይ አምስት ሴኮንዶች ግድም ላጭታለታለች።

ገንዘቤ ዲባባ [ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ / AP Photo]
ገንዘቤ ዲባባ [ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ / AP Photo]

ገንዘቤ በተጨማሪ ሌላ ድል ከሁለት ቀናት በሁዋላ ተጎናጽፋለች። በስፔን ከተማ በሣባዴል ባዳራሽ ውስጥ የ 3 ሺህ ሜትር በታሪክ ፈጣኑን ጊዜ በማጻፍ አጠናቃለች።

በሌላ የአትሌቲክስ ዜና፥ WADA ማለትም የዓለሙ የፀረ-ጉልበት ሰጪ መድሃኒት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ፥ ኬንያን ከ 2016 ቱ የሪኦ ኦሊምፒክ ለማገድ መዘጋጀቱን አስታውቋል። ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ 40 የኬንያ አትሌቶች የጉልበት ሰጪ መድሃኒት ምርመራ አለማለፋቸው ተረጋግጧል።

የእርስዎ አስተያየት

አስተያየቶችን ለማየት ይህንን ይጫኑ

XS
SM
MD
LG