ዩናይትድ ስቴትስና ናይጄሪያ የአሜሪካ ወታደራዊ አማካሪዎች በናይጄሪያ ሊመደቡ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ እየተነጋገሩ ናቸው

  • ሰሎሞን ክፍሌ
ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ሲዘግብ፥ የአሜሪካውያኑ ምደባ ሃሳብ የቀረበው፥ በአፍሪካ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ጦር አዛዥ በሆኑት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን በብሪጋዴር ጄኔራል ዶናልድ ቦልዱክ መሆኑን ጠቅሷል።

ዩናይትድ ስቴትስና ናይጄሪያ የአሜሪካ ወታደራዊ አማካሪዎች በናይጄሪያ ቦርኖ ክፍለ ግዛት ሊመደቡ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ እየተነጋገሩ ናቸው።

አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን ለባልደረባችን ጀፍ ሰልዲን እንደተናገሩት፥ ንግግሮቹ እየተካሄዱ ናቸው፥ ከውሳኔ ላይ ግን አልተደረሰም።

ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዛሬ ሲዘግብ፥ የአሜሪካውያኑ ምደባ ሃሳብ የቀረበው፥ በአፍሪካ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ጦር አዛዥ በሆኑት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን በብሪጋዴር ጄኔራል ዶናልድ ቦልዱክ መሆኑን ጠቅሷል።

ቦኮ ሓራም

በርካታ ቁጥር የሚኖራቸው አሜሪካውያኑ ወታደራዊ አማካሪዎች በቦርኖ ክፍለ ግዛት ዋና ከተማ በማዲጉሪ የሚመደቡት የናይጄሪያ ጦር ሠራዊት ፀረ-ሽብር የውጊያ ስልቱን በተሻለ መንገድ እንዲነድፉ ለመርዳት ነው ሲል ጋዜጣው ጨምሮ ዘግቧል።

ዩናይትድ ስቴትስ ባሁኑ ወቅት የቦኮ ሐራምን እንቅስቃሴ የሚከታተሉና በሰው አልባ አውሮፕላኖች ሥምሪት ላይ የተሠማሩ 250 ወታደሮች ካሜሩን ውስጥ እንዳላት ይታወቃል።

Your browser doesn’t support HTML5

ዩናይትድ ስቴትስና ናይጄሪያ የአሜሪካ ወታደራዊ አማካሪዎች በናይጄሪያ ሊመደቡ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ እየተነጋገሩ ናቸው