በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አራት የአሜሪካ የድሮን ሰፈሮች በምዕራብ አፍሪቃ ሀገሮች ተመሰረቱ


ድሮን ሰው አልባ ተዋጊ አይሮፕላን
ድሮን ሰው አልባ ተዋጊ አይሮፕላን

ክልላዊ ሀገሮች በቦኮ ሃራም ላይ የሚካሄዱትን ትግል ለመርዳት በሰሜን ካሜሩን የድሮን ማለትም የሰው አልባ ተዋጊ አይሮፕላን ሰፈር መስርታለች። ይህ እርምጃ ምን ያህል ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ጠበብት እየመረመሩ ነው።

የምዕራብ አፍሪቅ ሀገሮች በቦኮ ሐራም ላይ የሚያካሄዱትን ትግል ለመርዳት በአሁኑ ወቅት አራት የ አሜሪካ (United States) ድሮኖች ሰፈሮች ተመስርተዋል። ሶስቱ በኒጀር፣ ቡርኪና ፋሶና ቻድ ናቸው። አዲሱ የድሮንኖች ሰፍር በሰሜን ካሜሩን እየተመሰረት ነው። ሰሜን ካሜሩን ከናይጀርያ እየዘለቁ የቦኮ ሓራም አማጽያን ጥቃት ያዘወትሩበታል።

በናይጀርያ የ United States አምባሰደር የነበሩት ጆን ካምፕቤል የድሮኖች በአከባቢው መኖር ለውጥ ሊያመጣ ይችል እንደሆነ ይጠራጠራሉ። ናይጀርያ ከሲህ በፊት ከ United States ስታገኝ የቆየችውን የመረጃ አሰባሰብ አገልግሎት ብዙም አልተጠቀመችበትም ይላሉ።

“ነገሩ በጣም ወሳኝ የሚያደርገው ማናቸውም ሰፈሮች በአሜሪካ የጦር ተዋጊዎች ላይ የተመሰረቱ አለመሆናቸው ነው። መረጃ በመሰብሰብ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው። የችቦክ ሴት ተማሪዎች ከተጠለፉ በኋላ የ United States ሰራተኞች ወደ ናይጀርያ ተልከው ነበር። ሆኖም የስለለ ማሰባሰቡ ስራ ያስገኘው ጥቅም የለም።”

ሮበርት ማርቲን የተባሉት በሳምናታዊ የመከላከያ መጽሄት የሚሰሩ ተንታኝ በበኩላቸው አዎንታዊ አመለካከት አላቸው።

“መላ የክልሉ ወታደራዊ አዛዦችና ፕረዚዳንቶች ትልቅ እርዳታ አድርገው አይተውታል። ምክንያቱም ናይጀርያና ጎረቤቶችዋ ሃገሮች በቦኮ ሐራም ላይ በሚያካሄዱት ትግል የጎደላቸው ነገር ተገቢው የሰለላ አሰባሰብ ነበር። ብዙውን ጊዜ ራሳቸውን በመካለክል ተግባር ላይ ለመወሰን የተገደዱት ቦኮ ሐራም ቀጥሎ ስለሚያደርገው ነገር መረጃ ስለሌልቸው ነው። ስለሆነም የድሮኖች በካሜሩን መኖር ይረዳቸዋል ማለት ነው።”

ካምፕቤል ከዚህ በፊት ወታደሮቹ ስለሚያሰሙት የተጋነነ ድል ሲናገሩ ከቅርብ ወራት ወዲህ ስለ ቦኮ ሐራም መዳከም ብዙም የሚያስደስት ወሬ አልተሰማም ብለዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ያድምጡ።

አራት የአሜሪካ የድሮን ሰፈሮች በምዕራብ አፍሪቃ ሀገሮች ተመሰረቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:58 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG