በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ የደቀነውን የከፋ አደጋ ለመታደግ ጥሪ ቀረበ

አዲስ የተሰየሙት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄለ ቶየነን ሽሜድ(Helle Thorning-Schmidt)

“እዚህ ላይ እጅግ በጣም አሳሳቢው ጉዳይ፤ አሁን ማድረግ ያለብንን ፈጥነን ካላደረግን፤ የፈራነው እውን የመሆኑን አይቀሬነት ማወቃችን ነው። ያንዣበበውን አደጋ ለመታደግ፥ የኢትዮጵያ መንግስት የሚችለውን ሁሉ ቢያደርግም፤ እጅግ የከፋና መጠነ ሠፊ በመሆኑ ለብቻቸው ሁኔታውን ለመቀልበስ አይቻላቸውም።” የዓለም አቀፉ የሕጻናት አድን ድርጅት Save the Children ዋና ሥራ አስፈጻሚ Helle Thorning-Schmidt

ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ያልታየ በተባለው በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ከስድስት ሚልዮን በላይ ሕጻናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል፤ ሲል ዓለም አቀፉ የሕጻናት አድን ድርጅት Save the Children አስታወቀ።

በድርቅ በተመቱት አካባቢዎች ተዘዋውረው የጉዳቱት መጠን የተመለከቱት አዲስ የተሰየሙት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄለ ቶርኒንግ ሽሚዝ (Helle Thorning-Schmidt) ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃል፤ ድርቁ ባጠቃቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ቤተሰቦች ምግብና ውሃ ፍለጋ ከቀያቸው ርቀው ለመሄድ እየተገደዱ መሆናቸውን ገልጠዋል።

አዲስ የተሰየሙት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄለ ቶየነን ሽሜድ (Helle Thorning-Schmidt)

ሕጻናቱ እጅግ በጠናው የምግብ እጥረት ሳቢያ ለከፋ ስቃይና እንዲሁም ድርቁን ተከትሎ ለሚከሰቱ የተለያዩ ውሃ-ወለድ በሽታዎች እንዳይጋለጡ፤ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ፈጥኖ ምላሽ ሊሰጥ ይገባዋል፤ ሲሉም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አሳስበዋል።

“እልቂቱን ለመታደግ አሁንም ጊዜው አልረፈደም፤” ሲሉ ነው፤ ያንዣበበውን አደጋ አሳሳቢነት አጽንኦት በመስጠት የሴቭ ዘ ችልድረን (Save the Children) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄለ ቶየነን ሽሜድ፥ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅና ረሃብ አስመልክቶ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ የቋጩት።

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ የደቀነውን የከፋ አደጋ ለመታደግ ጥሪ ቀረበ

የአውሮፓ ኮሚሽን በኤል ኒኞ ምክኒያት ለተከሰተው ድርቅ ምላሽ €122.5 ሚልዮን እንደሚሰጥ ይፋ አደረገ