ቦኮ ሃራም ከጠለፋቸው "የቺቦክ ልጃገረዶች" መካከል ሁለተኛዋን እንዳስለቀቀ የጦር ሃይሉ አስታወቀ

  • ቪኦኤ ዜና

የናይጄሪያው ጽንፈኛ ቡድን ቦኮ ሃራም ከጠለፋቸው “የቺቦክ ልጃገረዶች“ መካከል ሁለተኛዋ ልጅ በቢዩ ከተማ ህክምና እየተደረገላት መሆኑን ታቋውል

የናይጄሪያው ጽንፈኛ ቡድን ቦኮ ሃራም ከሁለት ዓመታት ገደማ በፊት ከጠለፋቸው “የቺቦክ ልጃገረዶች“ መካከል ሁለተኛዋን አስለቀቅን ብሎ የጦር ሃይሉ የተናገረውን ልጃገረዶቹ እንዲለቀቁ የሚሟገቱ ወገኖች ሃሰት ብለውታል።

የናይጄሪያው ጽንፈኛ ቡድን ቦኮ ሃራም ከሁለት ዓመታት ገደማ በፊት ከጠለፋቸው “የቺቦክ ልጃገረዶች“ መካከል ሁለተኛዋን አስለቀቅን ብሎ የጦር ሃይሉ የተናገረውን ልጃገረዶቹ እንዲለቀቁ የሚሟገቱ ወገኖች ሃሰት ብለውታል።

የናይጄሪያ የጦር ሰራዊት ባወጣው መግለጫ በቦርኖ ክፍለ ሃገር ዳምቦአ አካባቢ ሐሙስ ያስለቀቃት ሳራ ሉካ የምትባል ልጅ ከቺቦክ የመንግስት ትምህርት ቤት ከተጠለፉት 219 ልጃገረዶች አንዷ ናት ብሎ ነበር።

የተጠለፉት የቺቦክ ልጃገረዶች ወላጆች ማህበር ሊቀመንበር ያኩቡ ንኬኪ ለአሜሪካ ድምጽ ሲናገሩ "ርግጥ ነው ሉካ የሚባሉ ሁለት ልጆች ከቺቦክ ተጠልፈዋል፣ ሴራ ሉካ የምትባለው ግን አይደለችም" ብለዋል።

በቦኮ ሀራም አማጽያን ከተጠለፉት 219 የሰሜን-ምሥራቅ ቺቦክ ልጃገረዶች አንዷ በህይወት ተለቀቀች

የሁለት መቶዎቹም ልጆች ዝርዝር መዝገብ በዕጄ አለ። ይቺ ልጅ የቺቦኳ አይደለችም ብለዋል።

የናይጄሪያ የጦር ሰራዊት በቦኮ ሃራም ቪዲዮዎች ሲታዩ የነበሩት ተጠላፊዎች እንደለበሱት ያለ ሰማያዊ ሂጃብ የለበሰች ልጅ ፎቶግራፍ ያወጣ ሲሆን ቢዩ ከተማ ህክምና እየተደረገላት መሆኑን ተናግሯል።

የመጀመሪያዋ የተለቀቀች የቺቦክ ልጃገረድ የአስራ ዘጠኝ ዓመቷ አሚና አሊ ማክሰኞ ዕለት ከአራት ወር ህጻን ልጇ ጋር በሲቪል የአካባቢው ጥበቃ ሰዎች ሳምቢሳ ደን ውስጥ ተገኝታለች።

የናይጄሪያ ፕሬዚደንት ማሀማዱ ቡሃሪ አሚናና እናቷን ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን የተቀሩትን የቺቦክ ልጃገረዶች ለማስለቀቅ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን ማለታቸው ተጠቅሷል።