የኬንያ ፍርድ ቤት 21 የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ አዘዘ

የኬንያ ካርታ

ፍለሰተኞቹ በህገ - ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ በመግባት ቢከሰሱም የኪያምቡ ፍርድ ቤት ዳኛ የፍልሰተኞቹን ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት የተለመደዉ ቅጣት ሳይጣልባቸዉ ወደ ሃገራቸዉ ይመለሱ በማለት ወሳኔ አስተላልፈዋል።

አንድ የኬንያ ፍርድ ቤት ከሳምንት በፊት በናይሮቢ በስተሰሜን ወደ 14 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በአገሪቱ ጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉት 21 የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች በነጻ ወደ ሃገራቸዉ እንዲመለሱ ወሰነ።

ፍለሰተኞቹ በህገ - ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ በመግባት ቢከሰሱም የኪያምቡ ፍርድ ቤት ዳኛ የፍልሰተኞቹን ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት የተለመደዉ ቅጣት ሳይጣልባቸዉ ወደ ሃገራቸዉ ይመለሱ በማለት ወሳኔ አስተላልፈዋል።

ፋይል ፎቶ - በኬንያ የሚገኝ ደዳብ የስደተኞች ካምፕ

አብዛኞቹ ፍልሰተኞች ለአቅም አዳም ያልደረሱ ልጆች እንደሆኑ ከፊሎቹ ደግሞ የቤተሰብ ሃላፊዎች፥ ታማሚዎችም እንዳሉባቸዉ ተመልክቷል። የድምጽ ፋይሉን በመጫን ዝርዝሩን ከገልሞ ዳዊት ዘገባ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኬንያ ፍርድ ቤት 21 የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ አዘዘ