የ"ቆሼ"ን አደጋ መንስዔ የሚያጠና ከሀገርና ከውጭ ሀገር ባለሞያዎች ተዋቀረ

  • መለስካቸው አምሃ
በኮልፌ ቀራኒዮ “ቆሼ” ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ በደረሰው አደጋ ምክንያት ጉዳት ያጋጠማቸውን ሰዎች የማቋቋሙ ሥራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሚፈፅመው የአስተዳደሩ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አስታወቁ፡፡

በኮልፌ ቀራኒዮ “ቆሼ” ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ በደረሰው አደጋ ምክንያት ጉዳት ያጋጠማቸውን ሰዎች የማቋቋሙ ሥራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሚፈፅመው የአስተዳደሩ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አስታወቁ፡፡

በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር ዛሬም 113 እንደሆነና ፍለጋውም እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ የአደጋውን መንስዔ እስከዛሬ ማወቅ እንዳልተቻለ ገልፀው ይሔንን የሚጣራ እና የሚያጠና ቡድን ከሀገርና ከውጭ ሀገር ባለሞያዎች እንደተዋቀረም አስታወቁ፡፡

መጋቢት 2/2009 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ ልዩ ስሙ “ቆሼ” ተብሎ በሚታወቀው ሥፍራ ምክንያቱ ምን ተለይቶ ባልታወቅ ሁኔታ በተደረመሰ የቆሻሻ ክምር በደረሰው ጉዳት ለተጎዱ ሰዎች የሚሰጠው እርዳታ እንደቀጠለ መሆኑን የከተማው አስተዳደር እየገለፀ ይገኛል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የ"ቆሼ"ን አደጋ መንስዔ የሚያጠና ከሀገርና ከውጭ ሀገር ባለሞያዎች ተዋቀረ