በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በ “ቆሼ” አደጋ የሞተው ሰው 72 ነው - ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ


ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ፤ የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር /ፎቶ ፋይል/
ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ፤ የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር /ፎቶ ፋይል/

የአደጋው መንሥዔ እየተጣራ መሆኑንና መንግሥት አሁን በማንም ላይ ውንጀላ አለማሰማቱን የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ገልፀዋል፡፡

በ “ቆሼ” አካባቢ ለደረሰው አደጋ ምክንያት የሆነው “በሥፍራው ላይ ውድቅዳቂና ቆሻሻ የሚለቅሙ ሰዎች እየሠረሠሩና እየቆፈሩ ክምሩን ስላናጉት ነው” ሲል የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትርን ጠቅሶ የፈረንሣይ የዜና ወኪል - ኤኤፍፒ ያሠራጨው ዘገባና በቪኦኤ የተላለፈው “ትክክል አይደለም፤ እኔ እንዲህ አላልኩም” ሲሉ የፅሕፈት ቤቱ ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለአሜሪካ ድምፅ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ አስተባብለዋል፡፡

የአደጋው መንሥዔ እየተጣራ መሆኑንና መንግሥት አሁን በማንም ላይ ውንጀላ አለማሰማቱን ዶ/ር ነገሪ አክለው ገልፀዋል፡፡

በአደጋው መሞታቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥርም ሰማንያ ሁለት ሳይሆን “ሰባ ሁለት ነው” ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

323 ሰዎችም በጊዜያዊ መጠለያ እየተረዳ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለቪኦኤ የሰጡት መግለጫ ሙሉ ዘገባ በረቡዕ ምሽት የራዲዮ ሥርጭታችን ይቀርባል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በ “ቆሼ” አደጋ የሞተው ሰው 72 ነው - ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:48 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG