በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዲስ አበባ “ቆሼ ሠፈር” በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 65 ደረሰ


በአዲስ አበባ “ቆሼ ሠፈር” በደረሰው አደጋ ሟቾች
በአዲስ አበባ “ቆሼ ሠፈር” በደረሰው አደጋ ሟቾች

ላዲሳባው የናዳ አደጋ አምነስቲ መንግሥትን ከሰሰ

አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ “ቆሼ ሠፈር” እየተባለ በሚጠራው ቆሻሻ ማስወገጃ ሥፍራ ላይ ትናንት በደረሰው የመናድ አደጋ የሞተው ሰው ቁጥር 65 መድረሱን የከተማዪቱ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ማምሻውን አስታውቀዋል፡፡

ከንቲባው ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ በአደጋው መሞታቸው የተረጋገጠው 45ቱ ሴቶች፤ ሃያው ወንዶች መሆናቸውን ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ግን እስከአሁን የደረሱበት ያልታወቀ ሰዎችን መፈለጉ እንደቀጠለ መሆኑን የፌደራሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉደዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ አመልክተዋል፡፡

ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አዲስ አበባ ውስጥ የቆሻሻ ክምር ተደርምሶባቸው ሕይወታቸው ስላለፈው ከስድሣ በላይ ኢትዮጵያዊያን ሰኞ ምሽት ላይ ባወጣው መግለጫ መንግሥትን ተጠያቂ አድርጓል፡፡

“ለዚህ ሊወገድ ይችል ለነበረ ከፍተኛ ቀውስ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂው መንግሥት ነው፡፡ መንግሥት የቆሻሻ መድፊያው መሙላቱን እያወቀ መጠቀሙን ቀጥሏል፡፡ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአካባቢው ሲኖሩም በቸልታ ሲመለከታቸው ነበር” ብለዋል የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካ ቀንድና የታላላቅ ሐይቆች አካባቢ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሙቶኒ ዋኜኪ፡፡

ዋኜኪ አክለውም “ሴቶችና ሕፃናት የሚገኙባቸው የናዳው ሰለባዎች በዚህ አደገኛ ሥፍራ ከመኖር የተለየ ምርጫም ያልነበራቸው ናቸው”ም ብለዋል፡፡

መንግሥት እስካሁን የት እንደደረሱ ያልታወቁትን ፈልጎ በማግኘት መኖሪያ እንዲሰጣቸውና ለቆሻሻው ክምር መደርመስ ምክንያት የሆነውን አጣርቶ ለጥፋቱ ተጠያቂ የሆኑትን ባለሥልጣናት ለፍርድ እንዲያቀርብ አምነስቲ አሳስቧል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ያዳምጡ።

በአዲስ አበባ “ቆሼ ሠፈር” በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 65 ደረሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:12 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG