የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ ለኢትዮጵያዊ ጀርመናውያን

ፋይል ፎቶ-ሁለት እናቶች ከሚያስተምሯቸው ጥቂት ተማሪዎቻቸው ጋር (ጀርመን ፍራንክፈርት)

በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ። ታድያ ከሀገር ርቀው እንደመኖራቸው ኢትዮጵያዊነታቸውን እንዳይረሱ ወላጆች ለልጆቻቸው የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ ለማስተማር ይጥራሉ።

ሁለት ኢትዮጵያውያን እናቶች ከራሳቸው ልጆች አልፈው ሌሎች ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዳጊ ወጣቶችን በማስማር ላይ ይገኛሉ። ማህሌት ደስታ እና ሶፍያ ረሻድ ይባላሉ። እነዚህ እናቶች የመማሪያ ቦታ አዘጋጅተው ሕፃናቱን በሳምንት አንድ ቀን ማስተማር ከጀመሩ አምስት አመታትን አስቆጥረዋል። መስታወት አራጋው ከፍራንክፈርት ጀርመን በስልክ አነጋግራቸዋለች። ከበታች ያለውን ድምፅ በመጫን አጠር ያለውን ቃለመጠይቅ ያድምጡ።

Teaching Ethiopian culture for Ethiopian- Germany kids

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ ለትውልደ ኢትዮጵያውያን