በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮምፒውተር ለወንዶች ወይንስ ለሴቶች?


ፋይል-ፎቶ አዳጊ ወጣቶቹ በኮምፒውተር ስልጠና ላይ
ፋይል-ፎቶ አዳጊ ወጣቶቹ በኮምፒውተር ስልጠና ላይ

በወጣት ሴቶችና በኮምፒውተር ቴክኖሎጂ የነበረውን ክፍተት ለመሙላት በዩናይትድ ስቴትስ ኒውዮርክ ከተማ አዲስ የስልጠና ዕቅድ መተግበር ጀመረ።

ዕቅዱ ለአመታት በወንዶች የበላይነት ተይዞ የቆየውን የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ በአዲሱ የኮምፒውተር ማዘዣ ቋንቋ (Computer Programs) ወጣት ሴቶችን ማሰልጠንና ስራ ላይ በማሰማራት ላይ ያተኮረ ነው። በዩናይትድ ስቴትስ በኒውዮርክ ከተማ ለ150 ወጣት ሴቶችና ወንዶች ሀካቱን ‘Hackathon” የተሰኘ የተግባር ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል። ስልጠናው በተለይም ለወጣት ሴቶች ከፍተኛ አትኩሮት በመስጠት የኮምፒውተርን ማዘዣ ቋንቋንና የቪዲዮ ቅኝት (ኮድን) በመጠቀም በመጠለያ የሚገኙ የተረሱና የተጣሉ የቤት እንስሳት ላይ ቪዲዮ እንዲሰሩ ይደረጋል።

በዚህ የስልጠና ወቅትም አዳጊ ወጣቶቹ የኮምፒውተር ቅኝት (ኮድ) እንዲማሩ፣ የሰሯቸውን ቪዲዮዎች በተለያዩ የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን፤ እንደ ፌስቡክ ወይም ኢንስታግራም ላይ እንዴት እንደሚያስቀምጡ ይማራሉ። ወጣቶቹ ግራፊክሱንና ስዕሎቹን ከመምረጥ ጀምሮ፤ ብዙ የኢንተርኔት ተመልካችን ለማሳደግ እንዴት እንደሚሰሩም ዕውቀትን ይቀስማሉ።

በስልጠናው ላይ የተካተቱት የኒዎርኮቹ ወጣት ሴቶች የተንገላቱና የተጣሉ እንስሳት ላይ በማተኮር የሰሩዋቸውን አጫጭር ቪዲዮዎች በርካታ የተመልካችን ቁጥር በማግኘት አሽናፊነትንም ተቀዳጅተዋል።

Online App Teaches Girls Computer Coding
Online App Teaches Girls Computer Coding

በድረ-ገፅ ላይ የተመሰረተው ይህ ስልጠና ደረጃ በደረጃ የኮምፒውተር ቅኝትን ያስተምራል። የዚህ ትምህርት ዋነኛ አላማውም ወጣት ሴቶችን ከወንዶች ጋር በእኩል በዚህ ዘርፍ ለማራመድ ማስቻል ነው። ተማሪዎቹን በማሰልጠን ላይ የሚገኘው ሚለር (Miller) የወጣት ሴቶቹ ብቃት ወደር አይገኝለትም በማለት አሞግሷቸዋል።

“እንዚህን ወጣት ሴቶች ከወንዶች ያንሳሉ የሚል እምነት የለንም። አሁንም የመሪነቱን ቦታ የያዙት እነሱ ናቸው ፤ ፕሮጀችቱንም በብቃት በመምራት ላይ ይገኛሉ።”

እነዚህ አዳጊ ወጣቶች የኮምፒውተር ብቃታቸውን በከፍተኛ ፍጥነት አሳድገዋል። ወደፊት በኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ከፍተኛውን ሚና እንደሚጫወቱም ሰልጣኞቹ ወጣቶች በራሳቸው እምነት አላቸው።

የቪኦኤው ባልደረባችን ማይክ ሱሊቫን የዘገበውን መስታወት አራጋው ታቀርበዋለች። ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያድምጡ።

ኮምፒውተር ለወንዶች ወይንስ ለሴቶች?
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:20 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG