የአፍሪካ ህብረት ልዑካን ቡድን በቡሩንዲ ሰላማዊ ድርድር ለመግፋት በያዘው ጥረት የቡጁምቡራ ጉብኝቱን ቀጥሏል

  • ሰሎሞን ክፍሌ
በአፍሪካ ህብረት ልዑካን ቡድን በቡሩንዲ ጉብኝት የሚያደርገው፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ለአሥር ወራት የዘለቀውን የሀሪቱን ግጭት ለማብቃት፥ የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ጥረት አካል የሆነውን ጉብኝት በዚህ ሣምንት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

የአፍሪካ ህብረት ልዑካን ቡድን በቡሩንዲው ግጭት የሚሳተፉ ወገኖችን ወደ ሰላማዊ ድርድር ለመግፋት በያዘው ጥረት፥ የቡጁምቡራ ጉብኝቱን ቀጥሏል።

በደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ጄኮፕ ዙማ የሚመራው የህብረቱ ልዑካንቡድን፥ ከመንግሥት፥ ከተቃዋሚና ከሲቪል ማህበረሰብ መሪዎች ጋር ይገናኛልተብሎ ይጠበቃል።

ይህ በአፍሪካ ህብረት ልዑካን ቡድን በቡሩንዲ ጉብኝት የሚያደርገው፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ለአሥር ወራት የዘለቀውን የሀሪቱን ግጭት ለማብቃት፥ የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ጥረት አካል የሆነውን ጉብኝት በዚህ ሣምንት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

በዓለምአቀፉ የቀውስ አስወጋጅ ቡድን የማዕከላዊ አፍሪካ ፕሮዤ ዳይሬክተር ሪቻርድ ሞንሴፍ ሲናገሩ፥ የአፍሪካ ህብረት ልዑካን ቡድን፥ ለሁለቱም ማለት ለፕሬዘዳንት ፕየር እንኩሩንዚዛ እና ለቡሩንዲ ታጣቂ የተቃዋሚ መሪዎችጠንካራ መልዕክት እንዲያስተላልፍ ድርጅታቸው መጠየቁን አስረድተዋል።

የልዑካኑ ቡድን ከሚያስተላልፋቸው መልዕክቶች መካከልም፥ ከቡሩንዲ ውጭ ድርድር ማካሄድና በግጭቱ የሚፈጸሙ ግድያዎች እንዲያቆሙ የሚጠይቁ ይገኙባቸዋል።

ቀደም ሲል በዩጋንዳው ፕሬዘዳንት ይዌሪ ሙሰቪኒ የተሞከረው የቡሩንዲየሰላም ንግግር ውጤት ሳያገኝ መቅረቱ ይታወቃል።

Your browser doesn’t support HTML5

የአፍሪካ ህብረት ልዑካን ቡድን በቡሩንዲ ሰላማዊ ድርድር ለመግፋት በያዘው ጥረት የቡጁምቡራ ጉብኝቱን ቀጥሏል