በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

Sorry! No content for 13 ዲሴምበር. See content from before

ሐሙስ 7 ዲሴምበር 2023

በረኀብ 111 ሰዎች እንደሞቱ የተገለጸበት የአፅቢ ወረዳ ነዋሪዎች አስቸኳይ ርዳታ እንዲደርስላቸው ተማፀኑ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:19 0:00

በትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ኣፅቢ ወረዳ፣ ባለፉት ሦስት ወራት፣ 111 ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ፣ የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የወረዳው የኢኮኖሚ ዘርፍ ሓላፊ አቶ ብርሃነ ገብረ፣ ባለፈው ክረምት፣ በወረዳው በቂ ዝናም ባለመዝነሙ ድርቅ እንደተከሠተ ጠቅሰው፣ በዚኽም፣ ከ82 ሺሕ በላይ ሕዝብ ለረኀብ እንደተጋለጠ ገልጸዋል፡፡

አኹን በወረዳው የተገኘው ምርት፣ ሕዝቡን ለመቀለብ የሚችለው ለ11 ቀናት ብቻ ነው፤ ያሉት ሓላፊው፣ የረኀብ አደጋው ለብዙዎች ሕይወት አስጊ እንደኾነ አመልክተዋል፡፡

የወረዳዋ ነዋሪዎችም፣ “ሞታችንን በዳጃችን ኾነን እየጠበቅን ነን፤” ሲሉ ረጂ አካላት አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርሷቸው ተማፅነዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በሰሜን ጎንደር ዞን ሦስት ወረዳዎች አራት ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:58 0:00

በዐማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በሦስት ወረዳዎች፣ በ2015/16 መኸር ምርት የተከሠተው ድርቅ ባስከተለው ረኀብ፣ አራት ተጨማሪ ሰዎች እንደሞቱ፣ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

በዞኑ በጃን አሞራ፣ በየዳ እና ጠለምት ወረዳዎች፣ ድርቁ ባስከተለው ጉዳት፣ ከወር በፊት 32 ሰዎች እንደሞቱ፣ በአካባቢው ባለሥልጣናት ተገልጾ እንደነበር ዩኒቨርሲቲው አስታውሷል፡፡ ተቋሙ በራሱ፣ ከአንድ ወር በላይ አደረግኹት ባለው ጥናት ደግሞ፣ ሕይወታቸው ያለፉት ወገኖች ቁጥር ወደ 36 ከፍ እንዳለና ከ72ሺሕ በላይ እንስሳትም እንደሞቱ፣ መምህር እና የጥናት ቡድኑ ሰብሳቢ ረዳት ፕሮፌሰር አምሳሉ አበጀ፣ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

በሦስቱ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 37 ቀበሌዎች፣ ከ107ሺሕ በላይ ሰዎች፣ አስቸኳይ የዕለት ምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፣ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ እስከ አኹን የደረሰው ርዳታ በቂ እንዳልኾነ የተናገሩት የጥናት ቡድኑ ሰብሳቢ፣ በመኸሩ ምንም ዐይነት ምርት ባለመገኘቱና እንስሳቱም በመሞታቸው፣ ነዋሪዎቹ ከዓመት እስከ ዓመት ርዳታ እንደሚያሻቸው አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG