በዐማራ ክልል፣ በ2015/16 መኽር ምርት የተከሠተውን ድርቅ ተከትሎ፣ ከ1ነጥብ5 ሚሊዮን በላይ ለኾኑ ተጎጂዎች የርዳታ እህል እንደተሰራጨ፣ የክልሉ የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ከፌዴራሉ እና ከክልሉ መንግሥት፣ እንዲሁም ከለጋሽ ድርጅቶች ከተገኘው ድጋፍ 60 በመቶ ያህሉን እንዳሰራጨ ገልጸዋል፡፡ ቀሪው 40 በመቶው ድጋፍ፣ በክልሉ ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት ማድረስ እንዳልቻለ ገልጸው፣ ተጎጂዎችን ለመታደግ ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሰሜን ጎንደር ዞን በጃን አሞራ ወረዳ “ክልል” በተባለ ቀበሌ የሚኖሩ አርሶ አደሮች፣ በቂ ድጋፍ እንዳላገኙ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።