አዲስ አበባ —
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች ስምንት(March 8) ወይም የካቲት 29 በሚከበርበት አጋጣሚ አራተኛዉ ዓለም አቀፍ የቡና ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዶ ነበር።
ጉባኤዉ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝና የአፍሪቃ ልማት ባንክ ልዩ መልክተኛ ጄራልዲን ፌሬዜር ሞልጌቲ ሴቶች ከወንዶች ሲነጻጸር ከቡናዉ ኢንዱስቲሪ የሚያገኙት ጥቅም እጅግ አናሳና ኢ-ፍትሃዊ መሆኑን አስምረዉበታል።
ጉባኤዉን የተከታተለዉ ዘጋቢአችን መለስካቸዉ አመሃ አጋጣሚዉን በመጠቀም በቡና ኢንዱስቲሪ ዉስጥ ከሚሰሩ ሴቶች አንዳንዶቹን አነጋግሯል። የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።