በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ገበያ የአሜሪካ ኩባንያዎች


የተባረከው ቡና (Blessed Coffee)
የተባረከው ቡና (Blessed Coffee)

በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያንና የንግድ ስራዎቻቸው በሁለቱ ሀገሮች የንግድ ግንኙነት መሪ ሚና መጫወት ይገባቸዋል ይላል ጥበቡ አሰፋ።

ዩናይትድ ስቴይትስ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የንግድና ምጣኔ ሀብት ግንኙነት ለማጠናከር ትፈልጋለች። በተለይ በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገሮች የውጭ መዋእለ-ንዋይ በመሳብ ላይ ናቸው።

ሆኖም ፈተናዎቹ ገና ከጅምሩ በርካታ መሆናቸውን ነው፤ ባለሙያዎች የሚያስረዱት። ከቼክኖሎጂ አንስቶ የአሰራር ብቃትና ቅልጥፍና፤ ብዙ ስራዎች የሚያስፈልጋቸው ናቸው።

በነዚህ ሁኔታዎች በኢትዮጵያ በመስራት ላይ ከሚገኙ አሜሪካዊያን ኩባንያዎች በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊያን ሰፊ ድርሻ አላቸው። በዛሬው ዝግጅት የተባረከው ቡና (Blessed Coffee) የተባለ ድርጅት አጋር መስራችን ይዟል።

ጥበቡ አሰፋ እንደሚለው ከሆነ፤ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያንና የንግድ ስራዎቻቸው በሁለቱ ሀገሮች የንግድ ግንኙነት መሪ ሚና መጫወት ይገባቸዋል ይላል።

በውጭ ያለው የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ “ገበያውን ያውቀዋል፣ ገንዘብም ለማሳተፍ ይችላል። እዚህ ያሉ የንግድ ተቋማት ኢትዮጵያ ካለው ጋር ቢተባበሩ፣ ሽርክና ቢፈጥሩ” የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ።

በኢትዮጵያ ገበያ የአሜሪካ ኩባንያዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:53 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG