በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮሚያ ወቅታዊ ኹኔታ ምን ይመስላል?


የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ንድፍን በመቃወም በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች በሕዳር ወር መግቢያ የቀሰቀሰው ተቃውሞ መንግሥት በቁጥጥር ስር አድርጌዋለሁ ማለቱ ይታወቃል።ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎች ክልሉ በስምንንት ወታደራዊ ቀጣናዎች ተከፋፋሎ እንደሚገኝ ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት የክልሉ ወቅታዊ ኹኔታ ምን ይመስላል? ከሁለት ማእዘናት የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮችን ትዝታ በላቸው አነጋግራለች።

አዲስ አበባን ወደ ኦሮሚያ ክልል ከተሞች ያስፋፋል የተባለውን የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ንድፍን በመቃወም በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች በሕዳር ወር መግቢያ ተነስቶ ስድስት ወሩን ባስቆጠረው የኦሮሚያ ተቃውሞ አብዛኛውን ቁጥር ወጣት ተማሪዎች የሚይዙት ከሁለት መቶ በላይ ዜጎች በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በሪፖርቶቻቸው ላይ አውጥተዋል።

በኢትዮጵያ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በበኩላቸው ይህን የሟቾች ቁጥር እስከ 400 ያደርሱታል። በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል በተሰነ መልኩ የዜጎችን መገደል አምኖ ተቃዋሚዎች ስምንት ፖሊሶችን በመግደል ይወነጅላል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ኦሮሚያ ውስጥ ለተካሄደው ተቃውሞ ምክንያቱ የመልካም አስተዳደር ጉድለት እንደኾን በመግለጽ መንግሥታቸውን በጥፋተኝነት መኮነናቸው የታወሳል።

የክልሉ ገዢ ፓርቲ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦ.ሕ.ዴ.ድ) ማስተር ፕላኑ ሥራ ላይ እንደማይውል ገልጾ ከ800 በላይ ጥፋተኛ ያላቸው አባላቱን ከሥልጣን ቢያስወግድም ተቃዋሚ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮበብዙ ሺሕ የሚገመቱ ሰዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። የሕዝቡ ተቃውሞ በመንግሥት ቁጥርር ስር ከዋለ በኋላ ግን በይፋ ባይረጋገጥም፤ የኦሮሚያ ክልላዊ አስተዳደር በስምንት ወታደራዊ ቀጣናዎች ተከፋልሎ እየተዳደረ እንደሚገኝ ይነገራል። ከተባረሩት ወጪ ያሉት የክልሉ ገዢ ፓርቲ ኦ.ሕ.ዴ.ድ

ባለሥልጣናትም በረጅም ስብሰባዎች ተጠምደው መዋል የመንግስት ሠራተኞችም ለወጉ ወደ ሥራ ቦታቸው ቢሄዱም የሚያከናውኑት ሥራ እንደሌለ ይነገራል። ትዊተር፣ ፌስቡክ ዋትስ አፕና ስካይፕ ስካይፕ የመሳሰሉ የኢንተርኔት ማኅበራዊ ድር በአብዛኛው የኦሮሚያ ክልል ከተሞች መዘጋታቸዉን የሰብአዊ መብት ድርጅት (Human Rights Watch) ከሳምንታ በፊት መግለጫ አውጥቷል።

በማልታ የሚገኙ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት [ፎቶ ፋይል - ሮይተርስ]
በማልታ የሚገኙ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት [ፎቶ ፋይል - ሮይተርስ]

ይህንን ሁኔታ ለማጣራትም በተለያየ ከተማ የሚኖሩ ሦስት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አባላትን አነጋግረናል። ከምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማ አቶ ሃማዶ፣ ከምስራቅ ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ አቶ ደገበሳ ዋቃዮ እንዲሁም ከምዕራብ ወለጋ ነጆ ከተማ አቶ ተስፋዬን ትዝታ በላቸው አነጋግራቸዋለች።

ሙሉውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

የኦሮሚያ ወቅታዊ ኹኔታ ምን ይመስላል?
please wait

No media source currently available

0:00 0:28:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ከእነርሱ ያገኘነዉን መረጃ ይዘንም ወደ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩንኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በፍቃዱ ተሰማን ለማግኘት ስልክ ደውለን ነበር። በሥራ ምክንያት አርብ ዕለት መልስ እንደሚሰጡን ገልጸዉ የነበረ ቢኾንም አሁንም በሥራ ምክንያት እንዳልተመቻቸው ገልጸው የፊታችን ሰኞ ቃለ ምልልስ ሊሰጡን ቃል ገብተዋል።

XS
SM
MD
LG