በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አራት የኦሮሞ ድርጅቶች ለመተባበር ተስማሙ


ዶ/ር በያን አሶባ /ፋይል ፎቶ/
ዶ/ር በያን አሶባ /ፋይል ፎቶ/

አራት ተቃዋሚ የኦሮሞ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሰሞኑን ባወጡት የጋራ የፕሬስ መግለጫ አስታውቀዋል።

አራት የኦሮሞ ድርጅቶች ለመተባበር ተስማሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:55 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አራት ተቃዋሚ የኦሮሞ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሰሞኑን ባወጡት የጋራ የፕሬስ መግለጫ አስታውቀዋል።

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፤ የተባበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር፤ የኦሮምያ ነፃ አውጭ ግንባር እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ዓላማ አድርገው የተነሡት የኢሕአዴግን አስተዳደር መታገልና መጣል መሆኑን አራቱንም ድርጅቶች ወክለው ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት ዶ/ር በያን አሶባ ተናግረዋል።

የፈጠሩት ኅብረት ማንኛውንም ዓይነት የትግል ሥልት የሚጠቀም እንደሆነ የገለፁት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሪ ዶ/ር በያን አሶባ ኢሕአዴግ የሰላማዊ ትግሉን መድረክ እንደዘጋውና አሁንም ቢሆን በድርጅቶቹ በኩል ለሰላማዊ ትግል ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

“ይሁን እንጂ የትግል ሥልት ልዩነት ኅብረታችንን እንዳያደናቅፍ በማለት ትኩረት ላለመስጠት ወስነናል” ብለዋል።

የትግላቸው መድረሻ የኢሕአዴግን ሥርዓት አስወግዶ የኢትዮጵያን የሽግግር መንግሥት መመሥረት እንደሆነ ዶ/ር በያን አመልክተዋል።

ከዶ/ር በያን አሶባ ጋር ለተደረገው ለሙሉው ቃለ-ምልልስ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG