ጄኔቫ —
በኢቦላ ክፉኛ ተጠቅተው የነበሩት የምዕራብ አፍሪቃ አገሮች ወረርሽኙ ዳግም ቢከሰት ለመከላከል በሚያስችል አቅም ራሳቸውን የተሻለ አዘጋጅተዋል፤ ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪቃ ዲሬክተር አስታወቁ።
ዲሬክተሩ ማትሺዲሶ ሞዊቲ በተለይ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ የ2014ቱ ኢቦላ ወረርሽኝ ዋነኛ ተጠቂዎች፥ ላይቤሪያ፥ ሴራሊዮንና ጊኒ በበሽታዎች ክትትል፥ የላቦራቶር ምርመራ እና የጤና ክብካቤ አገልግሎት አቅማቸውን በወጉ በማጎልበታቸው ለመሰል ድንገተኛ ሁኔታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት በሚያስችል ደረጃ ላይ ናቸው።
ሊሳ ሽላይ ከጄኔቫ ለአሜሪካ ድምጽ ያጠናቀረችውን ዘገባ አሉላ ከበደ አቅርቦታል።