በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢቦላና ኢትዮጵያ


ኢቦላና ኢትዮጵያ
ኢቦላና ኢትዮጵያ

ወደ ምዕራብ አፍሪካ የዘመቱት የጤና ባለሙያዎች ሲመለሱ የሃያ አንድ ቀናት ኳራንታይን ላይ እንደሚቀመጡ (ተነጥለው እንደሚቆዩ) ተገልጿል፡፡ እስከ ዛሬ በኢቦላ የተጠረጠረ ሰው ከውጭ ከገባ መንገደኛም ሆነ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:13:59 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያን ፀረ-ኢቦላ እንቅስቃሴዎች እያስተባበረ ያለው የኢንስቲትዩቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አቤል የሻነህ ለቪኦኤ እንደገለፁት ፍተሻው በቦሌና ትራንዚት በሚደረግባቸው ሌሎችም የሃገሪቱ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያዎች እና በወሰን አካባቢዎች መተላለፊዎች ላይ እየተካሄደ ነው፡፡

ምናልባት የኢቦላ ተጠርጣሪ ቢገኝ በሚል የተዘጋጁት አማኑኤል ሆስፒታል እና የካ የሚገኘው የጤና ጣቢያም ሃያ አራት ሰዓት ክፍት ሆነው እየተጠባበቁ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

ባለሙያዎቹም በየዕለቱ ሥልጠናና ክትትል እንደሚደረግላቸው አመልክተው ድንገት ለኢቦላ ተጋልጧል ተብሎ የሚጠረጠር ሰው ቢገኝ መደበኛ በሆኑ የሕክምና መንገዶች የተለያዩ ዓይነት የሕመም መገለጫዎችን እንደሚያክሙና እንደሚንከባከቡ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ በሌሎች ሃገሮች የሚሠራባቸው በሙከራ ላይ ያሉ መድኃኒቶች በእጃቸው የሌሉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ወረርሽኙ ወደ ተስፋፋባቸው የምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች የላከቻቸው 189 የጤና ባለሙያዎች ላይቤሪያና ሲየራ ሌዖን ደርሰው ተጨማሪ ሥልጠናዎችን እየወሰዱ መሆናቸውን አቶ አቤል ገልፀዋል፡፡

ኢቦላና ኢትዮጵያ
ኢቦላና ኢትዮጵያ

የሕክምና ባሙያዎቹ ግዳጅ ላይ የሚቆዩት ለሦስት ወራት መሆኑን እና ሲመለሱም ለጥንቃቄ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለሌሎችም ደኅንነት ሲባል ቢያንስ ለሃያ አንድ ቀናት ተነጥለው እንዲቆዩ እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡

በአንዳንድ መረጃዎች አለመሟላት ምክንያት ወደ ኋላ የቀሩት 21 ባለሙያዎችም በቅርቡ እንደሚሄዱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

አሁን ከዘመቱት መካከል 16ቱ ሃኪሞች፣ 71ዱ ነርሶች፣ 57ቱ የጤና ረዳቶች፣ 7ቱ ፋርማሲስቶች፣ ሰላሣው የመስክ የወረርሽኝ ተከታታይና አጥኚዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተጨማሪ ከአቶ አቤል የሻነህ ጋር የተደረገውን ቃለምልልስ የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG