የዑጋንዳ ባለስልጣናት የተቃዋሚ መሪዉ ኪዛ በሲጄ ትናንት ማክሰኞ በፓሪቲአቸዉ ማእከል በሚደረግ የጸሎት ስነስርዓት ላይ ሊገኙ እንደሚችሉነገርዋቸዉ ነበር። በሲጄወደ አንድ ቦታ ሲያመሩ ሕዝብ እርሳቸዉ መከተልየተለመደ ነዉ። ትናንትም ታዲያ ይሐዉ ነዉ የሆነዉ።
መሪዉ ከካምፓላ ወጣብሎ ከሚገኝ ቤታቸዉ ወደ መሃል ከተማ ሲያቀኑ ደጋፊዎቻቸዉ ተከተሏቸዉ። አንደኛ ደጋፊ በሲጄ እንደገና የታሰሩብን ሁኔታ ሲያስረዳ ገና መንገድ ስንጀምር ፓሊሶች የመረጥነዉን መንገድ ዘግተዉ እንዳናልፍ ከለከሉን። ወደ መሃል ከተማ የሚያመሩ መንገዶን ሁሉ ፓሊሶች አጠሩት ብሏል።
ፓሊሶቹ ወዲያዉ በሲጄን ቁጥጥር ስር አዉለዉ ከካምፓላ ወጣ ብሎ ወደሚገኝ ናጋላማ ፓሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል። አንድ የፓሊስ ቃል አቀባይ በሲጄ በህገ ወጥ ሰልፍ በመሳተፍ ነዉ የተከሰሱት ብሏል።
የበሲጄ እስራት በደጋፊዎቻቸዉ ዘንድ ቁጣና ቀቢጸ ተስፋና ቁጣን አስከትሏል አንዱ እንዲህ ገልጸዉታል። "በገዛ አገራችን ባእድ እንደሆን ነዉ የሚሰማን፣ አገሪቱ የእኛም እንዳልሆነች።በእዉነቱ ፕሬዚደንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ይህቺን አገር የግላቸዉ ብቻ እንዳደረጓት ነዉ የሚሰማን፣ ዑጋንዳ የዑጋንዳዉያን ሁሉ መሆኗ ቀርቶ የእርሳቸዉና የቤተሰባቸዉ ብቻ።" ብለዋል።
በሲጄ ከየካቲቱ የአገሪቱ ምርጫ በፊትም አያሌ ጊዜያት ተስረዉ እንደነበር ድምጽ ከተሰጠበት ቀን በኋላም ለአንድ ወር ተኩል እንደታሰሩ ይታወቃል።ያን ምርጫ ስልሳ በመቶዉን ድምጽ አገኘሁ በማለት ፕሬዚደንት ሙሴቪኒ ማሸነፋቸዉና ለአምስተኛ ጊዜ ስልጣን መቆጣጠራቸዉ ይታወሳል። በሲጄ 35 በመቶዉን ድምጽ በማግነት ሁለተኛ ተብሎ ነበር፥ ምርጫዉ የተጭበረበረ መሆኑን ቢናገሩም እንዲታሰሩ ሰለተደረገ በፍርድ ቤት ሊከራከሩ አልቻሉም። የድምጽ ፋይሉን በመጫን የትናንትናውን ሙሉ ዘገባ ያድምጡ።