በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈይሣ ሌሊሣ ከኢትዮጵያ፥ ሔላ ኪፕሮፕ ከኬንያ የ 2016ትን የቶክዮ ማራቶን አሸነፉ


በወንዶቹ ፈይሣ ሌሊሣ የቶክዮ ማራቶንን ያሸነፈው፥ የ 2014ቱን ሻምፒዮን ኬንያዊውን ዲክሰን ቹምባን ቀድሞ ነው።

ሔላ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትርፌ ፀጋዬ ተይዞ ከቆየው የኮርሡ ሬኮርድ ላይ አንድ ደቂቃ ግድም አንስታለት የገባችበት ሰዓት 2: 21: 23 ተመዝግቧል።

"ጥብጣቡን አልፌ እስከሄድኩበት ጊዜ ድረስ ለማሸነፌ እርግጠኛ አልነበርኩም” ያለችው ሔላ ኪፕሮፕ፥ ባለፈው ዓመት ያጠናቀቀችው በሁለተኝነት ነበር። አማኔ ጎበና ከኢትዮጵያ ሁለተኛ ሆናለች።

በወንዶቹ ፈይሣ ሌሊሣ የቶክዮ ማራቶንን ያሸነፈው፥ የ 2014ቱን ሻምፒዮን ኬንያዊውን ዲክሰን ቹምባን ቀድሞ ነው። የ 26 ዓመቱ ፈይሣ፥ ለመደመሪያ ጊዜ በማራቶን የሮጠው በ 2010 ሲሆን የትላንቱ 17ኛው ነው።

”ውሳኔው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቢሆንም ዛሬ በማሸነፌ ለ ሪዮ ኦሊምፒክ (Rio Olympic) ትኬት የቆረጥኩ ያህል ተሰምቶኛል” ብሏል ፈይሣ ሌሊሣ ከውድድሩ ፍጻሜ በኋላ ለጋዜጠኞች ሲናገር። ሙሉ ዘገባውን ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

ፈይሣ ሌሊሣ ከኢትዮጵያ፥ ሔላ ኪፕሮፕ ከኬንያ የ 2016ትን የቶክዮ ማራቶን አሸነፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:49 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG