በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ርዳታ የያዙ መኪናዎች ዛሬ ወደ ሶስት የሶሪያ ከተሞች ተንቀሳቅሰዋል

ምግብ፣ መድሃኒት እና የብርድ ልብሶች የያዙ በአጀብ ተጉዋዥ የጭነት መኪናዎች ዛሬ ሰኞ ወደ ሶስት የሶሪያ ከተሞች ተንቀሳቅሰዋል።

ምግብ፣ መድሃኒት እና የብርድ ልብሶች የያዙ በአጀብ ተጉዋዥ የጭነት መኪናዎች ዛሬ ሰኞ ወደ ሶስት የሶሪያ ከተሞች ተንቀሳቅሰዋል።

በመንግሥት ሃይሎችና በሽምቅ ተዋጊዎች ውጊያ በተጠመዱት ከተሞች ህዝቡ ለከባድ ችግር ተጋልጧል። ርዳታዎቹ ሊባኖስ ድንበር አጠገብ ወዳለችው ማዳያ ከተማና ቱርክ ወሰን ላይ ኢድሊብ ክፍለሀገር ወዳሉት ፉዋ እና ካፍራያ ከተሞች ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፉሳ (Fuaa) ፣ ካፍራያ (Kafraya)እና ማዳያ (Madaya) የሚባሉ ከተሞችን የሚያሳይ የሶርያ (Syria) ካርታ
ፉሳ (Fuaa) ፣ ካፍራያ (Kafraya)እና ማዳያ (Madaya) የሚባሉ ከተሞችን የሚያሳይ የሶርያ (Syria) ካርታ

የርዳታውን ጥረት በጋራ የሚያካሂዱት የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ፡ የሶሪያ ቀይ ጨረቃና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሆናቸው ታውቋል። የሶሪያ መንግሥት ርዳታ ወደ ከተሞቹ እንዲያልፍ ባለፈው ሳምንት መፍቀዱ ይታውሳል።

ርዳታ የጫኑት ተሽከርካሪዎች ተቃርበናል ብለው ከማስታወቃቸው በስተቀር ከተሞቹ ገብተናል አላሉም። የዜና ዘገባችንን ለማዳመት ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

ርዳታ የያዙ መኪናዎች ዛሬ ወደ ሶስት የሶሪያ ከተሞች ተንቀሳቅሰዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:13 0:00

XS
SM
MD
LG