በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአዲስ የሰላም ድርድር በፊት ሩስያ በሶርያ ላይ ያላትን አቋም አከረረች


የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርገይ ላቭሮቭ
የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርገይ ላቭሮቭ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋዜጣዊ ጉባኤ ላይ ይህን ያሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በመጪው አርብ ጄኔቫ ይጀመራል የተባለ አዲስ ዙር የሶርያ የሰላም ንግግር ለማካሄድ በሚዘጋጅበት ወቅት ነው።

የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርገይ ላቭሮቭ ሩስያ የሶርያው ፕረዚዳንት ባሸር አል-አሳድ ከስልጣን እንዲወርዱ አልጠየቀችም። የፖለቲካ ጥገኝነት እንደምትሰጣቸውም አልተናገረችም ሲሉ ዛሬ አስታውቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋዜጣዊ ጉባኤ ላይ ይህን ያሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በመጪው አርብ ጄኔቫ ይጀመራል የተባለ አዲስ ዙር የሶርያ የሰላም ንግግር ለማካሄድ በሚዘጋጅበት ወቅት ነው። የንግግሩ አላማ በሃገሪቱ የሚካሄደው ጦርነት አብቅቶ አዲስ ህገ-መንግስታና ምርጫ እንዲካሄ የሚያስችል የፖለቲካ ሽግግር ለማምጣት ነው።

የሩስያው ፕረዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ባለፈው ወር ባካሄዱት ቃለ መጠይቅ ፕረዚዳንት አሳድን መቀብል ችግር አይሆንም ብለው ነበር።

ሩስያ ፕረዚደንት ዓሳድን በመደገፍ ለአራት ወራት ያህል ያካሄደቸው የአየር ድብደባ በሶርያ ያለውን ሁኔታ ለመቀየር ረድቷል ሲሉ ሰገይ ላቭሮቭ አስገንዝበዋል።

XS
SM
MD
LG