No media source currently available
የደቡብ ሱዳን ሽምቅ ተዋጊ ቡድን መሪ የሪክ ማቻር ወታደሮች በታቀደው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ዛሬ ማክሰኞ ጁባ መግባታቸው አጠራጣሪ መሆኑ ተነገረ። ይህ መርሓ-ግብር ግን፣ ባለፈው ነሓሴ ወር በጁባው መንግሥትና በSPLM መካከል የተደረሰው ስምምነት ቁልፍ ነጥብ መሆኑ ይታወቃል።