ዋሽንግተን ዲሲ —
ባለፈው ዓርብ ሶማሊያ ጌዶ ክፍለ ሀገር ውስጥ የአል-ሸባብ ተዋጊዎች የደመሰሱት የኬኒያ ክፍለ ጦር ጥቃት እንደሚደርስ ማስጠንቀቂያ ደርሶት እንደነበር አንድ የሶማሊያ ጄነራል ተናገሩ።
የሶማሊያ ጦር ሰራዊት የጌዶ ክፍለ ሀገር አዛዥ የሆኑት ጄነራል አባስ ኢብራሂም ጉሬይ ለቪኦኤ የሶማሊኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል የኬንያው ጦር አዛዥ የመጀመሪያው ጥይት ከመተኮሱ ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ ሊያጠቋችሁ ነው ተብሎ ተነግሩዋቸው ነበር ብለዋል።
መረጃው ደርሶን ነግረናቸው ተዘጋጅተውበት ነበር ሲሉ ጄነራሉ አክለዋል።
ኬንያ ድንበር አጠገብ በምትገኝ የደቡባዊ ሶማሊያ ከተማ ኤል አዴ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የጦር ካምፕ በደረሰው ጥቃት ቢያንስ አርባ የኬንያ ወታደሮች መገደላቸውን የጌዶ ክፍለ ሀገር ምክትል አገረ ገዢ ገልጸዋል። የዜና ዘገባውን ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።