በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዞን9 ጦማሪያንና ጋዜጠኞች መከራና እንግልት እየደረሰብን ነዉ አሉ


የሲፒጄ የፕሬስ ነፃነት ሎሬቶች እማኝነት ሰጡ
የሲፒጄ የፕሬስ ነፃነት ሎሬቶች እማኝነት ሰጡ

ፍርድ ቤት በነፃ ያሰናበታቸው የኢትዮጵያ ጦማርያንና ጋዜጠኞች፥ መከራና እንግልት እየተፈጸመባቸው መሆኑን በኢንተርኔት ባሠራጩት ዜና አስታወቁ።

ፍርድ ቤት በነፃ ያሰናበታቸው የኢትዮጵያ ጦማርያንና ጋዜጠኞች፥ መከራና እንግልት እየተፈጸመባቸው መሆኑን በኢንተርኔት ባሠራጩት ዜና አስታወቁ። ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ ሕገ መንሥታዊ መብታቸው እንደታቀበ፥ በኤግዚቢት የተያዙ ንብረቶቻቸውም እንዳልተለቀቁላቸውና ወደ ስራቸዉ መመለስ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

የጦማርያኑ ጠበቃ፥ ድርጊቱ ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌን የጣሰና በሕግ የበላይነትም ላይ አሉታዊ አንደምታ ያለው ነው ብለዋል። ተፈጸሙ ለተባሉ የህግ ጥሰቶች መንግስት መልስ እንዲሰጥ የተደረገዉ ሙክራ እስካሁን አልተሳካም።

መለስካቸው አምሃ ዘግቦበታል የድምጽ ፋይሉን በመጫን ዝርዝሩን ያድምጡ።

የዞን9 ጦማሪያንና ጋዜጠኞች መከራና እንግልት እየደረሰብን ነዉ አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:04 0:00

XS
SM
MD
LG