ኬንያ —
የኬንያ ፖሊሶች ትናንት ናይሮቢ ውስጥ፥ የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ሥልጣን እንዲለቅ በጠየቁ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጋዝ መተኮሳቸውና ውኃ መርጨታቸው ተዘግቧል።
ተቃዋሚዎች በየሳምንቱ ሰኞ አደባባይ በመውጣት ሰልፍ እንደሚያካሂዱ ባለፈው ሳምንት ማስታወቃቸው ይታወሳል። ምርጫ ኮሚሽኑ ግን የተቃዋሚ ፓርቲዎቹን ጥያቄ አልቀበልም ብሏል።
ማህሙድ ዩሱፍ ተከታዩን አጭር ዘገባ ከሥፍራው አድርሶናል፣ ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል።