በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ላይ ስላሣለፈው ውሣኔ


ፋይል ፎቶ - የአውሮፓ ፓርላማ አባል አና ጎሜሽ እአአ 2012 (ፎቶ ሮይተርስ)
ፋይል ፎቶ - የአውሮፓ ፓርላማ አባል አና ጎሜሽ እአአ 2012 (ፎቶ ሮይተርስ)

የአውሮፓ ፓርላማ ከትናንት በስተያ ሐሙስ በኢትዮጵያ ላይ ያሣለፈውን ውሣኔ ለማስቀረት የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ መሥመሮች ጥረት ሲያደርግ እንደነበረ የፓርላማው አባል አና ጎምሽ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

የአውሮፓ ፓርላማ ከትናንት በስተያ ሐሙስ በኢትዮጵያ ላይ ያሣለፈውን ውሣኔ ለማስቀረት የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ መሥመሮች ጥረት ሲያደርግ እንደነበረ የፓርላማው አባል አና ጎምሽ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

የአውሮፓ ፓርላማ ባለፈው ሐሙስ ስትራስበርግ - ፈረንሣይ ተገናኝቶ በኢትዮጵይ ጉዳይ ላይ ሲከራከር በሶሻሊስቶቹና በዴሞክራቶቹ የቀረበውን ሃሣብ የተቃወሙት በቀኝ ክንፍ ያሉ ጥቂት ሰዎች ብቻ እንደነበሩ አና ጎምሽ ገልፀዋል፡፡

ከዚያ በተረፈ ግን ከስምንቱ የፓርላማው አባል የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ግዙፎቹን የአውሮፓ ሕዝብ ፓርቲ - ኢፒፒ እና የራሣቸውን ኤስ ኤንድ ዲ፣ እንዲሁም ሊበራሎችና ግሪኖችን ጨምሮ በሰባቱ ዋሃ ዋና የሚባሉ ቡድኖች፣ በእርሣቸው የሶሻሊስቶችና የዴሞክራቶች ቡድን የተረቀቀውንና የቀረበውን የውሣኔ ሃሣብ መደገፋቸውን ጎምሽ ገልፀዋል፡፡

የአውሮፓ ፓርላማ ካሣለፈው ባለአሥራ አምስት ነጥብ ውሣኔ መካከል፤ “የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እየወሰዷቸው ናቸው ያላቸውን ከመጠን ያለፉ የኃይል ጥቃቶች፣ የዘፈቀደና ሕገወጥ እሥራቶችን፣ የስቃይ አያያዞችና የነፃነት መረገጥን፣ የፕሬስ ነፃነት መታፈንን፣ በኢትዮጵያ አጥፍቶ ያለመጠየቅን ሁኔታ የአውሮፓ ፓርላማ በጥብቅ ያወግዛል” በሚል ይጀምራል፡፡

የአውሮፓ ፓርላማ አርማ(አሶሽየትድ ፕረስ/AP)
የአውሮፓ ፓርላማ አርማ(አሶሽየትድ ፕረስ/AP)

የኃይል እርምጃ፣ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎች፣ የፖለቲካ ማዋከብና ማሳደድ በአስቸኳይ እንዲቆሙ ይጠይቃል፡፡

መብቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በመጠየቃቸው ምክንያት የታሠሩ ያላቸው በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ይጠይቃል፡፡

በተፈፀሙት ግድያዎችና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ ተአማኒነት ያለው ግልፅና ወገንተኛነት የሌው ምርመራ እንዲካሄድ ይጠይቃል፡፡

መንግሥቱ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ሙሉ በሙሉ ለማቆም መወሰኑን የሚያሞግሰው ይኸው የውሣኔ ሠነድ ሁሉም ወገኖች የሚሣተፉበት ውይይት እንዲከፈት ጥሪ ያቀርባል፡፡

ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ዓለምአቀፍ ድንጋጌዎችንና ስምምነቶችን፣ የአፍሪካ ኅብረትንም የሰብዓዊ መብቶችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተርን እንድታከብር ይጠይቃል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን የሰብዓዊ መብቶች የመደራጀት፣ በሰላም የመሰብሰብ መብቶች ልዩ ራፖርን ኢትዮጵያ እንድትጋብዝና በሁኔታው ላይ ዘገባ እንዲያቀርብ እንድትፈቅድ ጠይቋል፡፡

ውሣኔው አክሎም ሃሣባቸውን በመግለፃቸው ብቻ ያላቸው ተይዘው ቀደም ሲልም ተይዘው እሥር ላይ የሚገኙ እንዲለቀቁ ጠይቋል፡፡

ከአና ጎምሽ ጋር በተደረገው ሙሉ ቃለ-ምልልስ ላይ የተዘጋጀውን ሪፖርት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የአውሮፓ ፓርላማን የውሣኔ ፅሁፍ ከዚህ ፋይል እናም ቪድዮውን፣ ይህንን ፋይል ተጭነው ይከተሉ፡፡ በተጨማሪም ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ላይ ስላሣለፈው ውሣኔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:58 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG