በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢራቅ ኃይሎች ሞሱልን ከአይስስ መልሶ ለመቆጣጠር ተጨማሪ የጦር ሠራዊት አባላት እንደምታሰማራ አስታወቀች


የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር አሽ ካርተር
የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር አሽ ካርተር

“ኢራቅ የምታካሂደው ዋና ፍልሚያ ሞሱል ላይ የሚካሄደው መሆኑን ሁሉም ያውቃል፤” ያሉት አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስቴር ከፍተኛ ባለ ሥልጣን፤ “ሞሱል ለኢራቅ ጦርነት የመጨረሻዋ የፍልሚያ ሜዳ ናት፤” ብለዋል የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር አሽ ካርተር።

የኢራቅ ኃይሎች ሞሱልን ከጽንፈኛው እስላማዊ ቡድን አይስስ (ISIS) መልሶ ለመቆጣጠር በያዙት ውጊያ ለማገዝ ዩናይትድ ስቴትስ ከሁለት መቶ በላይ ተጨማሪ የጦር ሠራዊት አባላትና ስምንት አፓቺ (Apache) ተዋጊ ሄሊኮፕተሮችን ማሰማራቷን፤ የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር አሽ ካርተር ባግዳድ ላይ ይፋ አደረጉ።

“ኢራቅ የምታካሂደው ዋና ፍልሚያ ሞሱል ላይ የሚካሄደው መሆኑን ሁሉም ያውቃል፤” ያሉት አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስቴር ከፍተኛ ባለ ሥልጣን፤ “ሞሱል ለኢራቅ ጦርነት የመጨረሻዋ የፍልሚያ ሜዳ ናት፤” ብለዋል።

የሞሱል ካርታ

የኢራቅ ኃይሎች በአክራሪው ቡድን ጠንካራ ይዞታ ስር የሚገኙ ቦታዎችን ለማስለቀቅ ባለፈው መጋቢት 15 የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ መክፈታቸው ይታወቃል።

የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር አሽ ካርተር፤ በኢራቅና በሶሪያ ከጽንፈኛው እስላማዊ ቡድን አይስስ ጋር በሚደረጉት ውጊያዎች አገራቸው በምታግዝባቸው መንገዶች ዙሪያ ከዩናይትድ ስቴትስ ጦር አዛዦችና የኢራቅ መሪዎችን ለመነጋገር ወደ ባግዳድ ያመሩት።

“ኢራቃውያን ለውጊያው የሚፈልጉትን እገዛ ከመጠየቅ አያመነቱም፤” ያሉት፤ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስቴር ከፍተኛ ባለ ሥልጣን፤ “የጦር ጀነራሎቻችንና ኮረሌኖቻችን ከኢራቃውያኑ ጋር ተቀምጠው በመመካከር ላይ ናቸው።” ብለዋል።

መከላከያ ሚንስትር ካርተር በበኩላቸው ባለፈው ቅዳሜ አረብ ኢሜሬት ላይ ለጋዜጠኞት በሰጡት አስተያየት፤ የሚቀርቡበትን የምክር ሃሳቦች ዋይት ሃውስ እንደሚያጸድቃቸው፤ ያላቸውን እምነት ገልጠዋል።

XS
SM
MD
LG