በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስላማዊ መንግሥት ቡድን አማጽያን በኢራቅ ወታደሮች ላይ ባካሄዱት ጥቃት 11 ገድለው ሌሎች በርካታ አቆሰሉ

አሶሽየትድ ፕረስ (Associated Press) እንደዘገበው፣ የአጥፍቶ ጠፊዎችና መንገድ ላይ የተጠመዱ ፈንጂዎችን ጨምሮ በተካሄደው በዚህ ጥቃት ወደ 30 የሚሆኑ ወታደሮች ቆስለዋል።

እራሱን ስላማዊ መንግሥት የሚለው ቡድን አማጽያ፣ በኢራቅ ወታደሮችና በትብብር በሚገኙ የጎሣ ተዋጊዎችን ላይ በምዕራባዊቷ ሃዲታል (Hadithal) ከተማ ዛሬ ሰኞ ባካሄዱት ጥቃት ቢያንስ 11 ገድለው ሌሎች በርካታ አቆሰሉ።

አሶሽየትድ ፕረስ (Associated Press) እንደዘገበው፣ የአጥፍቶ ጠፊዎችና መንገድ ላይ የተጠመዱ ፈንጂዎችን ጨምሮ በተካሄደው በዚህ ጥቃት ወደ 30 የሚሆኑ ወታደሮች ቆስለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዛሬ ሰኞ ማዕከላዊ ኢራቅ ውልስ በሚገኙ ሁለት የSuni መስጊዶች ላይ የደረሰ ፍንዳታ፣ ሌላ የሃይማኖት ጦርነት እንዳያስነሳ ከፍተኛ ስኝጋት መፍጠሩ ተሰምቷል።

ፍንዳታውን በመቃወም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በተገኙበት የባግዳድ ትይንተ-ሕዝብ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ Haider al-Abadi ባሰሙት ንግግር፣ እነዚህን «የአገር አንድነት የሚያናጉ» ያሏቸውን አጥቂዎች እገቡበት ገብተው እንደሚይዟቸውና ለፍርድ እንደሚያቀርቧቸው ቃል ገብተዋል።

እስካሁን ለጥቃቱ ኃፊነት የወሰደ ወገን አልተሰማም። የዜና ዘገባ አለን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የእስላማዊ መንግሥት ቡድን አማጽያን በኢራቅ ወታደሮች ላይ ባካሄዱት ጥቃት 11 ገድለው ሌሎች በርካታ አቆሰሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:05 0:00

XS
SM
MD
LG