የ አሜሪካ ወታደራዊ ሃይሎች ኢራቅን ከወረሩ ሰባት አመታት ተኩል ካለፉ በኋላ ፕረዚዳንት ኦባማ ወታደሮቹን ለአገልግሎታቸው አመስግነው የውጊያ ትልዕኮአቸው እንዳባቃ ገልጸውላቸዋል።
“የኢራቅ የነጻነት ተልዕኮ አብቅቷል። አሁን የኢራቅ ህዝብ የሀገሪቱን ጸጥታ የመጠበቅ ሃላፊነቱን ተረክቧል።”
ፕረዚዳንት ኦባማ የፕረዚዳንትነቱን ስልጣን ከተረከቡ ወዲህ ከመስርያ ቤታቸው ለሀገሪቱ ህዝብ ንግግር ሲያደርጉ ሁለተኛቸው ሲሆን ስለ ድል አልተናገሩም። ነገር ግን ወደ አዲስ ተልዕኮ እያመራን ነው ብለዋል።
“በ አሜሪካና እና በኢራቅ ታሪክ በነበረው ተጠቃሽ ምዕራፍ በኩል ሀላፊነታችንን ተወጥተናል። አሁን አዲስ ምዕራፍ የምንከፍትበት ጊዜ ነው።”
50,000 የሚሆኑ የአሜሪካ ወታደሮች፣ በኢራቅ ይቆዩና፣ እስከ መጪው አመት ማብቂያ ባለው ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ ተመድቧል። አዲሱ የ በአሜሪካ ተልዕኮ የኢራቅ የጸጥታ ሀይሎችን ማማከርና መርዳት ከጸረ አሸባሪነት ተልዕኮ ሀይሎች ጋር መተባበርና ሲቪሎችን መጠበቅ እንደሆነ ፐረዚዳንቱ አስገንዝበዋል።
የ አሜሪካ የኢኮኖሚ ማገገም ባዘገመበት በአሁኑ ወቅት ፐረዚዳንት ኦባማ ትኩረታቸውን ወደ ኢኮኖሚ ጉድይ አዙረዋል። የአሜሪካ ዋናው አስቸዃይ ተግባር የታጡትን በሚልዮኖች የሚቆጠሩ የስራ ዕድሎችን መመለስ ነው በማለት አስገንዝበዋል።