የተባበሩት መንግስታት ድርድት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ከኢትዮጽያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር ኢትዮጵያ በአካባቢ ጉዳዮች ስለምትጫወተዉ ገንቢ ሚና ተነጋግረዋል። ዋና ጸሀፊዉ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖችን በመሸምገል እንዲሁም በሶማሊያ ሰላም እንዲሰፍን ለምታደርገዉ ተሳትፎ አመስግነዋል።
በምእራብ አፍሪቃ ኢቦላ ከተሰፋፋባቸዉ አገሮች የጊኒ ፕሬዚደንት ወረርሺኙ አገራቸዉ ላይ እያደረሰ ያለዉን የኢኮኖሚ ቀዉስ ጠቅሰዉ ተናግረዋል። የአይሲል ሰፊ ግዛት የያዘባትና ዓለምአቀፍ ሥጋት የሆነባት የኢራቅ ፕሬዚዳንት እና ከመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት ተዋንያን የአንዷ ግዛት የፍልስጥዔም ፕሬዚዳንት እንዲሁም ተሰናባቹ የናሚቢያ ፕሬዚዳንትም የሃገራቸውን የሚሌኒየም የልማት ግቦች የስኬት ታሪክ፣ የአፋሪካን የኢቦላ፣ የፀጥታና የአየር ንብረት ፈተናዎች አንስተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከዘገባው ይከታተሉ።