No media source currently available
የሞያሌ ከተማን በከፊል የሚያስተዳድረው የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ነው እየያዘየሚያስራቸው ተብሏል። ከእነዚህ ወጣቶች አብዛኞቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ፖሊስ እስከ ሁለት ወር በእስር እንደሚያቆያቸዉ ይናገራሉ። ከምዕራብ ሸዋ የጉልበት ሥራ ፍለጋ ወደ ሞያሌ መጣሁ ያለ አንድ ወጣት፥ ከተማዋ በገባበት ማግሥት የመታወቂያ ወረቀት ለጠየቁት ፖሊሶች ቢያሳይም፥ ያለ ምንም ምክንያት ለ 2 ወር እንዳሠሩትና ወንጀል እንዳልሠራ ያስረዳል።