በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዎንታዊ ምላሽ ካልተገኘ መድረክ ውይይቱን ሊያቋርጥ እንደሚችል አስታወቀ


Prof. Beyene Petros
Prof. Beyene Petros

22 ፓርቲዎች በሚሳተፉበት ሸንጎ ላይ መደራደር እንደማይቻልና የመድረክ ፍላጎት ከገዢው ፓርቲ ኢሐዴግ እና ከመንግሥት ጋር ብቻውን መደራደር እንደሆነ የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጼጥሮስ ተናግረዋል።

በድርድሩ አካሄድ ላይ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ካላገኘ ውይይቱን ሊያቋርጡ እንደሚችሉ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ተናገሩ። መድረክ መሪ ተዳዳሪ ሆኖ እንዲቀርብ አለበለዚያም ጎን ለጎንና ብቻውን ከገዢው ፓርቲ ጋር እንዲደራደር ጥያቄ ሲያቀርብ ቆይቷል።22 ፓርቲዎች በሚሳተፉበት ሸንጎ ላይ መደራደር አይቻልም ብለዋል ፕሮፌሰር በየነ።

እስክንድር ፍሬው ዝርዝር ዘገባ አለው።

አዎንታዊ ምላሽ ካልተገኘ ውይይቱን ሊያቋርጡ እንደሚችሉ መድረክ አስጠነቀቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:04 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG