አዲስ አበባ —
ኢህአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሊካሄድ የታቀደው ድርድር በማን መመራት እንዳለበት እስካሁን ከስምምነት አልደረሱም፡፡
ኢህአዴግ በተሳታፊዎቹ ፓርቲዎች፣ ተራ በተራ እንዲመራ እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡ ሃያ ፓርቲዎች ደግሞ በገለልተኛ አደራዳሪ እንዲመራ እየጠየቁ ነው፡፡
ቀደም ባለው የቅድመ ድርድር ስብሰባ ድርድሩ ገለልተኛ በሆነና በፓርቲዎቹ ስምምነት በሚመረጥ አደራዳሪ መመራት እንዳለበት የጠየቁ ፓርቲዎች ነበሩ፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ