በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጂሃዲ ጆን በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው ሽብርተኛ መሞቱን የእስልምና መንግሥት ብሎ ራሱን የሚጠራው ቡድን አመነ


ፋይል ፎቶ - ሞሃመድ ኤምዋዚ ወይም "ጂሃዲ ጆን" በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው ሽብርተኛ በቪድዮ ከሳይት ኢንተል ግሩፕ (SITE Intel Group) የተገኘ ፎቶ
ፋይል ፎቶ - ሞሃመድ ኤምዋዚ ወይም "ጂሃዲ ጆን" በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው ሽብርተኛ በቪድዮ ከሳይት ኢንተል ግሩፕ (SITE Intel Group) የተገኘ ፎቶ

​​ባለፈው ህዳር ወር የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ ጂሃዲ ጆን ሶሪያ ውስጥ በተካሄደ የድሮን ጥቃት መገደሉን "በርግጠኝነት ለመናገር የሚያበቃ ምክንያት አለን" ማለቱ ይታወሳል።

ምዕራባውያን ታጋቾችን አንገት በመቅላት የሚታወቀው ጂሃዲ ጆን በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው አረመኔ ሽብርተኛ መሞቱን የእስልምና መንግሥት ብሎ ራሱን የሚጠራው ቡድን አመነ።

ከሳይት ኢንተል ግሩፕ (SITE Intel Group)የተባለው የስለላ መረጃ ክትትል ዌብሳይት እንዳለው ሽብርተኛው ቡድን በእንግሊዝኛ መጽሄቱ ላይ የነፍሰ ገዳዩን መታሰቢያ አውጥቱዋል።

ምዕራባውያን ታጋቾችን አንገት በመቅላት የሚታወቀው ጂሃዲ ጆን በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው አረመኔ ሽብርተኛ ከሳይት ኢንተል ግሩፕ (SITE Intel Group) ቪድዮ የተገኘ ፎቶ

ባለፈው ህዳር ወር የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ ጂሃዲ ጆን ሶሪያ ውስጥ በተካሄደ የድሮን ጥቃት መገደሉን "በርግጠኝነት ለመናገር የሚያበቃ ምክንያት አለን" ማለቱ ይታወሳል።

እውነተኛ ስሙ ሞሃመድ ኤምዋዚ የሆነው ጂሃዲ ጃን የአረብ ዝርያ የእንግሊዝ ዜጋ ሲሆን ፊቱን በጥቁር ጭምብል ሸፍኖ ምዕራባውያንን እያወገዘ የታጋቾችን አንገት ሲቀላ በቪዲዮ የሚታየው ነው። አሜሪካውያን ጋዜጠኞንና እንግሊዛውያን የርዳታ ሰራተኞችን ጭምር ከዚህ በፊት አርዷል። የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

ጂሃዲ ጆን በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው ሽብርተኛ መሞቱን የእስልምና መንግሥት ብሎ ራሱን የሚጠራው ቡድን አመነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:15 0:00

XS
SM
MD
LG