በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሪታንያ ከአይስስ (ISIS) የተሰራጨ ነው ተብሎ የታመነን ቪዲዮ በመመርመር ላይ ትገኛለች


የብሪታንያው ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከአይስስ (ISIS) የተሰራጨ ነው ተብሎ የታመነን አንድ ቪዲዮ በመመርመር ላይ መሆኑ ተሰማ።

የብሪታንያው ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከአይስስ (ISIS) የተሰራጨ ነው ተብሎ የታመነን አንድ ቪዲዮ በመመርመር ላይ መሆኑ ተሰማ።

ቪዲዮው የሚመረመረው፣ እስላማዊ መንግሥት ነኝ ባዩ ነውጠኛ ቡድን፣ ሦርያ ውስጥ ተቀምጠው ለእንግሊዝ የሚሰልሉ «አምስት ዦሮ ጠቢዎችን ገድያለሁ» ብሎ ይፋ ያደረገው ነው ስለተባለ መሆኑም ታውቋል።

ይህ የ10 ደቂቃ ቪዲዮ፣ የተባሉት ሰላዮች በእርግጥም እንደሰለሉና የተለያዩ ፎቶግራፎችም ማንሳታቸውን ያመኑ አስመስሎ አስቀምጧል ነው የተባለው።

ከታጣቂዎቹ አንደኛው፣ «ግድያው፣ ኢራቅና ሦርያ ውስጥ በነበሩ እስላማዊ ነውጠኞች ላይ ጥቃት እንዲካሄድ ላደረጉት ለእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን መልዕክት ነው» ብሎ መናገሩም በቪዲዮው ላይ ተሰምቷል።

ይኸው ታጣቂ አክሎም፣ እስላማዊው መንግሥት አንድ ቀን እንግሊዝን ተቆጣጥሮ በሸሪያ ህግ መሠረት እንደሚያስተዳድራትም ፈክሯል። የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

ብሪታንያ ከአይስስ (ISIS)የተሰራጨ ነው ተብሎ የታመነን ቪዲዮ በመመርመር ላይ ትገኛለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:59 0:00

XS
SM
MD
LG