በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ያዚዲ የሚባለው ሃይማኖታዊ ማህበረሰብ አይስስን ወደ ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት እንዲመራ ተማጸነ


የያዚዲ ሃይማኖታዊ ማህበረሰብ አባል
የያዚዲ ሃይማኖታዊ ማህበረሰብ አባል

"በጅምላ ይገድላል በጅምላ በባርነት ይይዛል ይሄ በጅምላ ማጥፋት ጂኖሳይድ መፈረጅ አለበት" የሃያ ንድ አመትዋ ናዲያ ሙራድ ባሲ ጣሃ።

ኢራቅ ውስጥ የእስልምና መንግስት ነኝ ባዩ ቡድን አግቶ ወከባ ሲፈጽምባት የነበረች አንዲት ያዚዲ የሚባለው ናሳን ሃይማኖታዊ ማህበረሰብ አባል ወጣት ዓለም አቀፉ ማሃበረሰብ የሽብርተኛውን ቡድን ወንጀሎች ወደአለም ዓቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት እንዲመራ ተማጸነች።

የሃያ ንድ አመትዋ ናዲያ ሙራድ ባሲ ጣሃ ትናንት ረቡዕ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጣት ምክር ቤት ባደረገችው ንግግር ቡድኑ በያዚዲዎች ላይ የጅምላ ፍጅት እየፈጸመ ነው። "በጅምላ ይገድላል በጅምላ በባርነት ይይዛል ይሄ በጅምላ ማጥፋት ጂኖሳይድ መፈረጅ አለበት" ብላለች።

አይሲስ የሚፈጽመውን ህገ ወጥ የሰዎች ማጋዝ በተመለከተ በተነጋገርው የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ወጣትዋ ባቀረበችው ጠንካራ ተማጽኖ በአይሲስ ተዋጊዎች እጅ የደረሰባትን በግድ በሚስትነት መያዝ፡ ወሲባዊ ጥቃት በጅምላ መደፈር ዘርዝራለች።

XS
SM
MD
LG